አቤቱ ነፍሴ
Abietu Nefsie
2010 · ትራክ 6 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አምላኬ ፊትህን መቼ አየዋለሁ
ውዴ ሆይ አንተስ ጋር መቼ እደርሳለሁ
አዝማች · Chorus
አቤቱ ነፍሴ አንተን ናፈቀች (፪x)
እንደ ዋላ ውኃ እንደተጠማች (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ውኃም እንጨትም በሌለበት
ነፍሴ ተጠማች የአምላኳን ፊት
ሥጋዬም ናፍቃ በምድረበዳ
ኃይልህን ክብርህን እንድታይ ወዳ
አዝማች · Chorus
አቤቱ ነፍሴ አንተን ናፈቀች (፪x)
እንደ ዋላ ውኃ እንደተጠማች (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ወዳንተ ወዳንተ እገሰግሳለሁ (፬x)
በመኝታዬ አስብሀለሁ
ማለዳ ቀትር አወራሀለሁ
ነፍሴ ከኋላ ተከተለችህ
ውዴ ወዳጄ ፍቅሬ አለችህ
አምላክ ወዴት ነው ዘወትር ሲል
እምባዬ በዝቶ ምግብ ሲሆነኝ
ወደ ምሥጋና ማደሪየህ ልግባ
ነፍሴ እንድትጠግብ አንተን አስባ
አዝማች · Chorus
አቤቱ ነፍሴ አንተን ናፈቀች (፪x)
እንደ ዋላ ውኃ እንደተጠማች (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ