ኢየሱሴ የምታልፈው
Eyesusie Yemetalfew
2010 · ትራክ 10 · 5:05 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አለም ሁሉ በእርሱ እያረፈ
ይኼ ጌታ በዚህ እያለፈ
ዝም አልልም እጮሀለሁ
የዳዊት ልጅ እለዋለሁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እየሱሴ የምታልፈው
የቆጠርከኝ እኔን ከሰው
ባክህ ንካኝ አይኔን/ግባ ቤቴን ፈውሰው (፪x)
አዝማች · Chorus
ዝም አልልም አታልፍም/ደርሶልኝ ቀኔ
ዝም አልልም ሳይበራ/ልትበራ አይኔ
ዝም አልልም አዳኜ መጥቶ
አየዋለሁ አይኔ ተከፍቶ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የሚጋፋ ግን የማይነካ
የሚከፋው ለሰው ሲሳካ
ተው ቢለኝም አልተውም እኔ
ጨልሞብኝ አይለቅ ዘመኔ (፪x)
አዝማች · Chorus
እየሱሴ የምታልፈው
የቆጠርከኝ እኔን ከሰው
ባክህ ንካኝ አይኔን/ግባ ቤቴን ፈውሰው (፪x)
ዝም አልልም አታልፍም/ደርሶልኝ ቀኔ
ዝም አልልም ሳይበራ/ልትበራ አይኔ
ዝም አልልም አዳኜ መጥቶ
አየዋለሁ አይኔ ተከፍቶ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እርሱ ጠርቶ ምን ይለመናል
ብር ወርቅማ ሰውም ይሰጣል
ልከተልሀ ፈውስ አይኔን
መብራት የኔን ሰውነቴን (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
በሰፈሬ በመንደሬ
ሰምቻለሁ መልካም ወሬ
መታሰሬ መታወሬ
ታሪክ ይሁን ያብቃ ዛሬ
አንዴ ልይህ አንተን ዛሬ (፪x)
አዝማች · Chorus
እየሱሴ የምታልፈው
የቆጠርከኝ እኔን ከሰው
ባክህ ንካኝ አይኔን/ግባ ቤቴን ፈውሰው (፪x)
ዝም አልልም አታልፍም/ደርሶልኝ ቀኔ
ዝም አልልም ሳይበራ/ልትበራ አይኔ
ዝም አልልም አዳኜ መጥቶ
አየዋለሁ አይኔ ተከፍቶ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ