Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሰላም አለኝ

Selam Alegn

2010 · ትራክ 7 · 6:00 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሰላም አለኝ ከአንተ ጋር ሰላም አለኝ (፬x)

ሀዘን የሚገፍ ሰላም ሰላም አለኝ

አእምሮን የሚያልፍ ሰላም ሰላም አለኝ

አልሰኝም ቅር ሰላም ሰላም አለኝ

ልቤ አይሰበር ሰላም ሰላም አለኝ

ሰላም አለኝ ከአንተ ጋር ሰላም አለኝ (፬x)

በልዑል መጠጊያ እንደሚኖር ሰው (፪x)

ሁሉን በሚችለው እሸሸጋለሁ (፪x)

አምላክ ጥላ ውስጥ ምን እሆናለሁ (፪x)

አምላክ ጥላ ስር ምን ያገኘኛል (፪x)

አምላክ ጥላ ውስጥ መታመኛዬ (፪x)

አምላክ ጥላ ስር ሰላም ደስታዬ (፪x)

ሰላም አለኝ ከአንተ ጋር ሰላም አለኝ (፬x)

ነገስ አልልም ሰላም ሰላም አለኝ

ለእራሱ ይጨነቅ ሰላም ሰላም አለኝ

ክፋት ቢሰንቅ ሰላም ሰላም አለኝ

አይበርደኝ አልሞቅ ሰላም ሰላም አለኝ

ሰላም አለኝ ከአንተ ጋር ሰላም አለኝ (፬x)

አምላክ ጥላ ውስጥ ምን እሆናለሁ (፪x)

አምላክ ጥላ ስር ምን ያገኘኛል (፪x)

አምላክ ጥላ ውስጥ መታመኛዬ (፪x)

አምላክ ጥላ ስር ሰላም ደስታዬ (፪x)

ሰራዊት ቢሰፍር ሰላም ሰላም አለኝ

ሰልፍ ቢነሳ ሰላም ሰላም አለኝ

ምድር ቢናወጥ ሰላም ሰላም አለኝ

ሰላም አለኝ ሰላም ሰላም አለኝ (፪x)

ሰላም አለኝ ከአንተ ጋር ሰላም አለኝ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ