እኔስ አለኝ
Enies Alegn
2010 · ትራክ 1 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አንደበቴ አይፈታም ሥራ
ለምሥጋና ስለ ተሰራ
የልቤ ሀሳብ የአፌ ቃል
አማረልኝ ዕልልታ ይዟል
አዝማች · Chorus
እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሁሉም ነገር አላፊ ነው አምልኮ ግን ዘላቂ ነው
የሚታየው አላፊ ነው አምልኮ ግን ዘላቂ ነው
የሚሰማው አላፊ ነው አምልኮ ግን ዘላቂ ነው
ክብር ዝና አላፊ ነው አምልኮ ግን ዘላቂ ነው
አሃ አሃ አንተን ፈልጌ አሃ አሃ ውስጤማ ናፍቆ
አሃ አሃ ፍቅርህ ገባብኝ አሃ አሃ በልቤ ዘልቆ
አሃ አሃ ይኸው ሽብሸባ አሃ አሃ ለስምህ ጉዳይ
አሃ አሃ የእኔስ እልልታ አሃ አሃ ይሂድ ወደላይ
አዝማች · Chorus
እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አንተ በሰራኸው አልወስድም ምሥጋና
ልቤን ከፈትኩ እንጂ ምን አደረኩና
አንተ በሰራኸው አልወስድም ምሥጋና
እንኳን ተቀንሶ መቼ ይበቃና
ይኸው (፪x) ዕልልታው ይኸው (፪x)
ይኸው (፪x) ሽብሸባው ይኸው (፪x)
ይኸው (፪x) እልልታው ይኸው (፪x)
ይኸው (፪x) አምልኮው ይኸው (፪x)
ባለቤቱ የምሥጋና እግዚአብሔር እርሱ አለና
ባለቤቱ የዕልልታ ይኸውልህ ይኸው ጌታ
ባለቤቱ የምሥጋና እግዚአብሔር እርሱ አለና
ባለቤቱ የዕልልታ ይገባሀል የእኔ ጌታ
መሻቴ የእኔማ ደስታ የአምልኮ ሽታ
አላማ የመፈጠሬ ለዚህ ነው ላምልክ አብሬ
ቅሬታ የለም ትካዜ ምስጋናን ባሰብኩኝ ጊዜ
አዝማች · Chorus
እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
አንደበቴ አይፈታም ሥራ
ለምሥጋና ስለ ተሰራ
የልቤ ሀሳብ የአፌ ቃል
አማረልኝ ዕልልታ ይዟል
አዝማች · Chorus
እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ (፬x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ሁሉም ነገር አላፊ ነው አምልኮ ግን ዘላቂ ነው
ገንዘብ ንብረት አላፊ ነው አምልኮ ግን ዘላቂ ነው
ስልጣን ሹመት አላፊ ነው አምልኮ ግን ዘላቂ ነው
ዘውዱ ንግሱ አላፊ ነው አምልኮ ግን ዘላቂ ነው
አዝማች · Chorus
እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ (፬x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ባለቤቱ የዕልልታ ይኸውልህ ይኸው ጌታ
ባለቤቱ የምሥጋና እግዚአብሔር እርሱ አለና
ባለቤቱ የዕልልታ ይገባሀል የእኔ ጌታ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ