ሲታመኑት የሚታመን
Sitamenut Yemitamen
2010 · ትራክ 13 · 6:07 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ሲታመኑት የሚታመን
ቃሉን ደግሞ የማይበላ
የነገሩትን የማይረሳ
የለመኑትን የማይነሳ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ኢየሱስ ሁልጊዜ እውነተኛ
ኢየሱስ እርሱ ለእኔ አለኛ
ኢየሱስ አይወድቅ ቃሉ መሬት
ኢየሱስ ታማኝ ላመኑበት
ሲታመኑበት ታማኝ (፬x)
ሲታመኑበት ታማኝ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ረዳት በሌለበት በዚያ ቦታ
ማን ተስፋ ይደረጋል ያለጌታ
ዓይኔን የጣልኩበት አንድ ዋሴ
ጥያቄዬ ገባው እየሱሴ
ኢየሱሴ (፪x) የጥያቄ ሁሉ መልሴ
ኢየሱሴ (፪x) ዋስ ጠበቃ ነው ለነፍሴ
አዝማች · Chorus
ሲታመኑት የሚታመን
ቃሉን ደግሞ የማይበላ
የነገሩትን የማይረሳ
የለመኑትን የማይነሳ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እየሱስ ሁልጊዜ እውነተኛ
እየሱስ እሱ ለኔ አለኛ
እየሱስ አይወድቅ ቃሉ መሬት
እየሱስ ታማኝ ላመኑበት
ቁጥር 4 · Verse 4
ልቤን ወረሰና ወራሽ ሳይኖር
እንደኔማ ቢሆን ባልተገባኝ
ታሪኬን የሚያውቁ ጉድ ይበሉ
ሲያወጣኝ ሲያገባኝ እንደ ቃሉ
እንደ ቃሉ (፪x) ዝንፍ አይል አሰራሩ
እንደ ቃሉ ጌታ ቃሉ
አይሳሳት ስራው ምክሩ
አዝማች · Chorus
ሲታመኑት የሚታመን
ቃሉን ደግሞ የማይበላ
የነገሩትን የማይረሳ
የለመኑትን የማይነሳ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ኢየሱስ ሁልጊዜ እውነተኛ
ኢየሱስ እርሱ ለእኔ አለኛ
ኢየሱስ አይወድቅ ቃሉ መሬት
ኢየሱስ ታማኝ ላመኑበት
ቁጥር 6 · Verse 6
በቃሉ የሰፈረው እንደዚህ ነው
የእኔ ነገር እኮ በእጁ ነው
አልሞትም በህይወት ልኑር እንጂ
ከበቂ በላይ ነው የአንተ እጅ
የአንተ እጅ (፪x) ከሰው በላይ የሚመች
የአንተ እጅ (፪x) መች ይጥላል ሚያነሳ እንጂ
አዝማች · Chorus
ሲታመኑት የሚታመን
ቃሉን ደግሞ የማይበላ
የነገሩትን የማይረሳ
የለመኑትን የማይነሳ (፪x)
ቁጥር 7 · Verse 7
ኢየሱስ ሁልጊዜ እውነተኛ
ኢየሱስ እርሱ ለእኔ አለኛ
ኢየሱስ አይወድቅ ቃሉ መሬት
ኢየሱስ ታማኝ ላመኑበት
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ