አዳነኝ
Adanegn
2010 · ትራክ 8 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ታሪክ አይደል ተረት
የሰራው በኔ ሕይወት
ብዙ ሀያላን እያሉ
ወዶ አዳነኝ በቃሉ
አዝማች · Chorus
አዳነኝ ወደደኝና አወጣኝ ወደ ሰፊው ስፍራ
ቁጥር 2 · Verse 2
አዳነኝ (፪x) ወደ ሰፊው ስፍራ አወጣኝ
አዳነኝ (፪x) ወደ ፍቅሩ መንግስት አገባኝ
አስቤው አይደልም አቅጄ (፪x)
አስቦልኝ እንጂ ተወድጄ (፪x)
የሞት ወጥመድ ቀርቦ ሊይዘኝ
ኪዳኑ ምህረቱ አዳነኝ (፪x)
የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት
ለእኔ ግን መቆም የመኖሬ/የመዳኔ ምክንያት
አዝማች · Chorus
አዳነኝ (፪x) አወጣኝ ወደ ሰፊው ስፍራ
ቁጥር 3 · Verse 3
አዳነኝ (፪x) ወደ ፍቅሩ መንግስት አገባኝ
እንደማልችል አውቆ በራሴ (፪x)
ታዳጊ ሆነላት ለነፍሴ (፪x)
ነጠቀኝ ከአፋፉ ከሞት (፪x)
አረገኝ ካህኑ ለፍቅሩ መንግስት (፪x)
አዝማች · Chorus
አዳነኝ (፪x) አስቀመጠኝ ጐኑ በአብ ቀኝ
ቁጥር 4 · Verse 4
አዳነኝ (፪x) የመንግስቱ ወራሽ አረገኝ
ታሪክ አይደል ተረት
የሰራው ለኔ ሕይወት
ብዙ ኃያላን እያሉ
ወዶ አዳነኝ በቃሉ
አዝማች · Chorus
አዳነኝ ወደደኝ አወጣኝ ወደ ሰፊው ስፍራ
ቁጥር 5 · Verse 5
አዳነኝ (፪x) ወደ ሰፊው ስፍራ አወጣኝ
አዳነኝ (፪x) ወደ ፍቅሩ መንግስት አገባኝ
የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት
ለእኔ ግን መቆም የመኖሬ/የመዳኔ ምክንያት (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ