Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አልሞትኩም

Almotkum

2011 · ትራክ 8 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አይሁዶች ሃሳባቸው በሃማ እጅ መጥፋታቸው (፪x)

ማን እንደሚሞት ላልታወቀ መስቀያው ተሰርቶ አለቀ

ጆሮውን ለሰማይ ሰጥቶ የምድሩን ለሃማ ትቶ

ከአባቱ ያዳመጠ ያው በክብር ተገለጠ

የሰማው ከላይ ነው (፫x)

የሰማው ከላይ ነው (፫x)

ሰሞኑን ሰማሁ ክፉ ወሬ

በተወለድኩበት በአገሬ

ትንሹ ዮሴፍ በሕይወት አለ

አባትዬው ሰምቶ ጉድ አለ

እረ እኔ አልሞትኩም አለሁ

እረ እኔ አልሞትኩም (፫x)

ይሄ ነው ተነስ ቀባው የኔን ልብ ያሳረፈው (፪x)

ነብዩ ቀብቶት ወጣ ቅባቱ ነገር አመጣ

ከጐልያድ ጭንቅ ያሳረፈውን መልሶ ጠላት ሆነዉ

የእግዚአብሔር ቃሉ አልፈረሰም ሳኦል ሞቶ ዳዊት ነገሠ

የሰማው ከላይ ነው (፫x)

የሰማው ከላይ ነው (፫x)

ሰሞኑን ሰማሁ ክፉ ወሬ

በተወለድኩበት በአገሬ

ትንሹ ዮሴፍ በሕይወት አለ

አባትዬው ሰምቶ ጉድ አለ

እረ እኔ አልሞትኩም አለሁ

እረ እኔ አልሞትኩም (፫x)

ስኬቴ ያስከፋቸው ውድቀቴ ደስ ያላቸው (፪x)

ላልሞተ ሰው አስለቅሶ በቁሜ አፈር አልብሰው

ልብ ሊስቅ እንደለመዱ ለታይታ ሙሾ ወረዱ

ከሰማይ በቃቹህ አለ ለዘሩት ዋጋ ከፈለ

የያዘኝ እጁ ነው (፫x)

የያዘኝ እጁ ነው (፫x)

ሰሞኑን ሰማሁ ክፉ ወሬ

በተወለድኩበት በአገሬ

ትንሹ ዮሴፍ በሕይወት አለ

አባትዬው ሰምቶ ጉድ አለ

እረ እኔ አልሞትኩም አለሁ

እረ እኔ አልሞትኩም (፫x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ