Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እንዲህም አለ

Endihem Ale

2011 · ትራክ 5 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አምላክ ከሆነ ለእኛ ከሞተ

ከሰማይ ወርዶ እኛን ከአዳነ (፪x)

ኧረ እንዲህም አለ አምልኮ ኧረ እንዲህም አለ (፪x)

ኧረ እንዲህም አለ ዕልልታ ኧረ እንዲህም አለ (፪x)

ኢየሱስን ያድናል ብለው

ኢየሱስን አምላክ ነው ብለው

ኢየሱስን ጌታዬ ብለው

ኢየሱስን አባት ነው ብለው

ሰይጣን ምን አቃጠለው

ሰይጣን ስሙ አቃጠለው (፪x)

ኧረ ይሁን ሽብሸባ ኧረ ይሁን (፪x)

ከእግዚአብሔር ሌላ ሌላ ሌላ

አምላክ አናውቅም ሌላ ሌላ (፪x)

ከኢየሱስ ሌላ ሌላ ሌላ

አማላጅ አናውቅም ሌላ (፪x)

አምላክ ከሆነ ለእኛ ከሞተ

ከሰማይ ወርዶ እኛን ከአዳነ (፪x)

ኧረ እንዲህም አለ አምልኮ ኧረ እንዲህም አለ (፪x)

ኧረ እንዲህም አለ ዕልልታ ኧረ እንዲህም አለ (፪x)

አንድ ጥያቄ አለኝ ሲኦል ለሚሉት

እስኪ እነማን ናቸው አንተን የረቱት

ይዘመር ይነገር ይሰማ ይህ ወሬ

ሞቶ የተነሳ የለም እስከዛሬ

ይባል በዘሬ ይመለክ ዛሬ (፪x)

ኧረ ይሁን ሽብሸባ ኧረ ይሁን (፪x)

ከእግዚአብሔር ሌላ ሌላ ሌላ

አምላክ አናውቅም ሌላ (፪x)

ከኢየሱስ ሌላ ሌላ ሌላ

አማላጅ አናውቅም ሌላ (፪x)

አምላክ ከሆነ ለእኛ ከሞተ

ከሰማይ ወርዶ እኛን ከአዳነ (፪x)

ኧረ እንዲህም አለ አምልኮ ኧረ እንዲህም አለ (፪x)

ኧረ እንዲህም አለ ዕልልታ ኧረ እንዲህም አለ (፪x)

ኧረ እንዲህም አለ አምልኮ ኧረ እንዲህም አለ (፪x)

ኧረ እንዲህም አለ ዕልልታ ኧረ እንዲህም አለ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ