Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ማደሪያህ እንዴት ያማረ ነው

Maderiyah Endiet Yamare New

2011 · ትራክ 3 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

"(ሃሌሉያ) ሉዑል ሆይ ማደሪያህ እንደምን የተወደዱ ናቸው

(ሃሌሉያ) እናመሰግንሃለን (ሃሌሉያ) (፫x) ማደሪያህ ውብ ነው (ሃሌሉያ) (፬x)"

ማደሪያህ እንዴት ያማረ ነው (፪x)

መንፈስህ እንዴት ያማረ ነው (፰x)

የገባውን ቃልኪዳኑን ያላጠፈ

ሲሸከመኝ ለዘመናት ያልሰነፈ

በድካሜ የያለኝን ሳይለውጠው

ስደርስበት ሁሉንም እንዳለኝ ነው (፪x)

ማደሪያህ እንዴት ያማረ ነው (፪x)

መንፈስህ እንዴት ያማረ ነው (፰x)

"ያማረ ነው ማደሪያህ

አንተ ያለህበት ጌታዬ

ያማረ ነው መኖሪያህ ያማረ ነው"

የትንቢቱን ቃል ሲፈጽመው በየተራ

ተሳስቶ አንዴ ለሰው መች አወራ

አወይ አባት ኀጢአቴን ተሸክሞ

በአደባባይ እወደዋለሁ ይላል ቆሞ (፪x)

እንዴት ከአምልኮ እነሳለሁ

ከአምልኮ የሚሻል ምንድን ነው

እንዴት ከጸሎት እነሳለሁ

ከጸሎት የሚያስነሳኝ ምንድን ነው

እንዴት መዝሙር አቆማለሁ

ከመዘመር የሚሻል ምንድን ነው

መዋያዬ ቅድስተ ቅዱሳን

ማደሪያዬ ቅድስተ ቅዱሳን (፰x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ