ትክክል ነው
Tekekel New
2011 · ትራክ 9 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ቢሆንም ባይሆንም አምልኮዬን አላቆምም (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
አዳዲስ መዝሙር ለእርሱ ነውና (ምሥጋና ምሥጋና)
ለታላቅነቱ (ምሥጋና ምሥጋና) (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ታሞ አዘነ ሞቶ አለቀሰ
የሰው እርዳታ መች ከዚህ አለፈ
ሲታመም ቀርቶ ሞቶ ቢደርስ
ሬሳ አይተናል ሲቀሰቀስ
አዝማች · Chorus
ቢሆንም ባይሆንም አምልኮዬን አላቆምም (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የቤቱን ትልቅ ኤልያብን ትቶ
ቀቡልኝ ካለ እረኛውን ጠርቶ
ያዕቆብን ወዶ ኤሳውን ከጠላ
ሲረፍድ ይገባል የጌታ ስራ
ቁጥር 4 · Verse 4
ትክክል ነው ትክክል ነው (፮x)
ቁጥር 5 · Verse 5
የሰማይ መስኮት ቢከፈት እንኳን
በአንድ ቀን ይሄ እንዴት ይሆናል
ንጉሡ እምቢ ቢል ትንቢት አዳምጦ
ሳይበላ ሞተ በሰው ተረግጦ
አዝማች · Chorus
ቢሆንም ባይሆንም አምልኮዬን አላቆምም (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
አዳዲስ መዝሙር ለእርሱ ነውና (ምሥጋና ምሥጋና)
ለታላቅነቱ (ምሥጋና ምሥጋና) (፪x)
ትክክል ነው ትክክል ነው (፮x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ