ማን ልበለው
Man Lebelew
2011 · ትራክ 13 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ገና ከጅምሩ በዚህ ሂድ ያለኝ
ወጥቼ እስክመለስ ዐይን ዐይኔን ያየኝ
ጥርሴ እየሳቀ ልቤ እያለቀሰ
የኖርኩበት ዘመን በክብር ተካሰ (፪x)
አዝማች · Chorus
አባት ብለው አይገልጸውም
ወዳጅ ብለው አይገልጸውም
ረዳት ብለው አይገልጸውም
ኧረ እኔስ ማን ልበለው (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ገዳዬ እንዳያየኝ እጁ ላይ ተኝቼ
ደጅ አድሬ አላውቅም ከእቅፉ ወጥቼ (፪x)
እዩ አባት (፪x) ነፍሱን እስከመስጠት (፪x)
መንገዴን አጥሮታል ዙሪያዬ ግድግዳ
እረ እንዴት ጭንቅ ነው የመከራው ናዳ (፪x)
ከቤት ውስጥ ትንሽ ነኝ ዘመድ የለኝ ደግሞ
የአለእድሜዬ ክብር አሳየኝ አቁሞ (፪x)
አዝማች · Chorus
አባት ብለው አይገልጸውም
ወዳጅ ብለው አይገልጸውም
ረዳት ብለው አይገልጸውም
ኧረ እኔስ ማን ልበለው (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ቀን ይማከራሉ ሌሊት ያደባሉ
ህልም የነገርኳቸው አብረውኝ የበሉ ወንድሞች ተባሉ
ሄጄ ሂጄ ደክሞኝ መንገድ ላይ ወድቄ
ደግሞ እንዳይገድሉኝ በእጁ ትደብቄ እዛው ተደብቄ
እዩ አባት (፪x) ነፍሱን እስከመስጠት (፭x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ