እድለኛ ነኝ
Edelegna Negn
2011 · ትራክ 1 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እድለኛ ነኝ እኔ (፪x) እድለኛ
አዲስ እድሜ ከሰማይ የሰጠኛ ነኝ እኔ እድለኛ
እድለኛ ነኝ እኔ አዲስ እድሜ ከሰማይ የሰጠኛ
ለአምልኮ ማን ይቀድመኛል
ቁጥር 1 · Verse 1
መስቀሉ ለእኔ ነው የተሰራልኝ
ስሞት ህዝብ ሊያየኝ ሊሳለቅብኝ
ለካ ተዐምራት በጣም የሚያምረው
እግዚአብሔር ከሰማይ ሲያረፋፍድ ነዉ
ባልጠፋ ሰዓት በሌሊት ተነስቶ
ያገላብጥ ጀመር መዝገቤን ጐትቶ
የፋርስና ሜዶን ህግ ተገልብጧል
ሃማ መሞቻዉን አሳምሮ ሰርቷል
የሚሞተውን ሰው አትሞትም ብሎታል
የመኖሪያ ፈቃድ ኢየሱስ ሰጥቶታል
በእርሱ እድሜ አይቀለድም (፬x)
በራዕዩ ምክንያት ጉድጓድ ውስጥ ቢጣልም
እግዚአብሔር አላለም መንገድ ላይ አይቀርም
መቼ ጓዳ ቀረ በጉድጓድ ተውጦ
አደባባይ ወጥቷል ነገር ተገልብጦ
በግብጽ በአካባቢው በአገር ሰው እያለ
ተሸጦ የመጣው ዙፋን ላይ ቁጭ አለ
ፈርኦን በቤቱ ቢኖርም ባይኖርም
ጌታ ንጉሥ ካለህ መሾምህ አይቀርም
አዝማች · Chorus
እድለኛ ነኝ እኔ (፪x) እድለኛ
አዲስ እድሜ ከሰማይ የሰጠኛ ነኝ እኔ እድለኛ
እድለኛ ነኝ እኔ አዲስ እድሜ ከሰማይ የሰጠኛ
ለአምልኮ ማን ይቀድመኛል (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እድለኛ ነኝ እኔ አዲስ እድሜ ከሰማይ የሰጠኛ
ለአምልኮ ማን ይቀድመኛል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ