Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሰይጣን ውሸቱን ነው

Seytan Weshetun New

2011 · ትራክ 10 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ፀሐይ ዘምበል ብላ አመሻሹ ላይ ነኝ

ችግሬ እያለ ሚነጋ መሰለኝ

ለካ አምላኬ ሰምቷል ጠላቴ እየዛተ

የተዘጋጋው በር አውቆ ተከፈተ

ሰይጣን ውሸቱን ነው (፪x) ትሞታለህ ያለው (፪x)

ኢየሱስ እውነቱን ነው (፫x) አትሞትም ያለው (፪x)

በሞትና በእኔ አንድ እርምጃ ቀርቶ

ምን ረዳኝ አትበል ከረፈደ መጥቶ

አምላክህ ሲነሳ ሲያንጐዳጉድ ከላይ

መከራህ በጓዳ ክብርህ በአደባባይ

ይደርደር ይደርደር በገና

ዕድሜ ቀጠለልኝ ይገባዋልና

ሌላ ሌላ ምሥጋና (፬x)

ፈሮን ከሁአላ ቀይ ባሕር ከፊት ነው

ግብጽ አይመለሱም ኢየሱስ ኢየሱስ ብለው

በአራቱም አቅጣጫ ሞት እየቸኮለ

የገዳዬ ገዳይ ከሰማይ ብቅ አለ

ሰይጣን ውሸቱን ነው (፪x) ትሞታለህ ያለው (፪x)

ኢየሱስ እውነቱን ነው (፫x) አትሞትም ያለው (፪x)

ይደርደር ይደርደር በገና

ዕድሜ ቀጠለልኝ ይገባዋልና

ሌላ ሌላ ምሥጋና (፬x) (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ