እኔ ነኝ
Enie Negn
2011 · ትራክ 11 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የልቡን በር ያንኳኳዉ
ደርሶ ስሙን ያደሰዉ
ሰው ላድርግህ ሰው ሁን ያለው
ያ ምስኪን ልጅ ሥሙ ማነው (፪x)
አዝማች · Chorus
እኔ ነኛ ከመንገድ ላይ ያነሳኛ
እኔ ነኝ እኔ ነኝ በምህረቱ የቆምኩኝ
እኔ ነኝ እኔ ነኝ በምህረቱ ያገዘኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
የልቤን በር የአንኳኳዉ
ሰላም ለአንተ ይሁን የአለዉ
ሰው ሊያደርገኝ ወደደና ቤቴ ገባና (፪x)
የልቡን በር የአንኳኳዉ
ደርሶ ስሙን ያደሰዉ
ሰው ላድርግህ ሰው ሁን ያለው
ያ ምስኪን ልጅ ስሙ ማነው (፪x)
አዝማች · Chorus
እኔ ነኛ ከመንገድ ላይ ያነሳኛ
እኔ ነኝ እኔ ነኝ በምህረቱ የቆምኩኝ
እኔ ነኝ እኔ ነኝ በምህረቱ ያገዘኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
ብዙ ኀጢአቴን ሁሉ ትቶ
እንደገና እድል ሰጥቶ
በምህረቱ ያቆመኝ
ያ ሰው እኔ ነኝ (፪x)
የልቡን በር የአንኳኳዉ
ደርሶ ስሙን ያደሰዉ
ሰው ላድርግህ ሰው ሁን ያለው
ያ ምስኪን ልጅ ስሙ ማነው (፪x)
አዝማች · Chorus
እኔ ነኛ ከመንገድ ላይ ያነሳኛ
እኔ ነኝ እኔ ነኝ በምህረቱ የቆምኩኝ
እኔ ነኝ እኔ ነኝ በምህረቱ ያገዘኝ
ቁጥር 4 · Verse 4
እድል ሰጪ ለወደቀ
በሰዎች ዘንድ ለተናቀ
ይዘምራል ዛሬ ቆሞ
በእጁ ታክሞ (፪x)
የልቡን በር ያንኳኳዉ
ደርሶ ስሙን ያደሰዉ
ሰው ላድርግህ ሰው ሁን ያለው
ያ ምስኪን ልጅ ስሙ ማነው (፪x)
አዝማች · Chorus
እኔ ነኛ ከመንገድ ላይ ያነሳኛ
እኔ ነኝ እኔ ነኝ በምህረቱ የቆምኩኝ
እኔ ነኝ እኔ ነኝ በምህረቱ ያገዘኝ
ቁጥር 5 · Verse 5
ትረዳለህ ታግዛለህ አባት ትሆናለህ
የወደቀውን አንስተኀው
ይዘምራል ያ ትንሽ ሰው
መዝሙር ለአንተ ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ