አልተወውም
Altewewm
2013 · ትራክ 13 · 5:37 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
"አልተወውም አለቀውም መድሃኒቴን
የሰላሜን ጌታ እረፍት የሰጠኝን
ጌታ ኢየሱስን ኦሆሆ"
አዝማች · Chorus
አልተወውም አለቀውም መድሃኒቴን
የሰላሜን ጌታ እረፍት የሰጠኝን
ቁጥር 2 · Verse 2
ጌታ ኢየሱስን (፪x)
መግቢያ መውጫ አጥቼ ስንከራተት በዓለም
አጽናናኝ ኢየሱስ ነይ የእኔ ነሽ አለኝ
ጥሪውንም ሰማሁ ሕይወቴም ረካሁ
መቅበዝበዜም ቀረ ነፍሴም ተደሰተች
አዝማች · Chorus
አልተወውም አለቀውም መድሃኒቴን
የሰላሜን ጌታ እረፍት የሰጠኝን
ቁጥር 3 · Verse 3
ጌታ ኢየሱስን
ኃያሉ አምላክ ነው ለእኔ የደረሰው
ማቄን የቀደደ እንባዬን ያበሰው
ሰላም ኧረፍት ሰጥቶኝ መድሃኒት የሆነኝ
ተስፋዬን አድሶ በቃሉ ያጸናኝ
አዝማች · Chorus
አልተወውም አለቀውም መድሃኒቴን
የሰላሜን ጌታ እረፍት የሰጠኝን
ቁጥር 4 · Verse 4
ጌታ ኢየሱስን ኦሆሆ
ለነፍሴ እረፍት ሆነ ቀለለ ሸክሜ
መጨነቄ ቀረ ፈሰሰ ሰላሜ
ፀጋን አለበሰኝ ነውሬንም ሸፈነ
ልገዛለት እንጂ እርሱን እንዴት ልተው (፪x)
አዝማች · Chorus
አልተወውም አለቀውም መድሃኒቴን
የሰላሜን ጌታ እረፍት የሰጠኝን
ቁጥር 5 · Verse 5
ጌታ ኢየሱስን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ