Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እውነተኛ አምልኮ

Ewnetegna Amleko

2013 · ትራክ 14 · 4:12 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አመጣጤም ባያምርም እግዚአብሔር ይወደኛል

አኗኗሬም ባያምርም እግዚአብሔር ይወደኛል

አፍቃሪ ባይኖረኝም እርሱ ግን ይወደኛል

ወላጆች ባይኖሩኝም እግዚአብሔር አለ ማለቢ. (1) .

ወላጆች ባይኖሩትም አመጣጧ ባያምርም

ልጆች ግን የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው

እነሱን ተንከባክቦ በፍቅር ማሳደግ

የአምላክን ስጦታ ማክበር ነው

ንጹህ የሆነ ነውር አልባ

ጌታን የሚያስከብር አምልኮ

እውነተኛ የሆነ አገልግሎት

በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይሄ ነው

አፍቃሪ ባይኖረውም አኗኗሯ ባያምርም

እግዚአብሔር በልጆጅ ላይ አላማ አለው

ፍቅር እያሳዩ እነሱን ማሳደግ

የጌታን አላማ ከግብ ማድረስ ነው

ንጹህ የሆነ ነውር አልባ

ጌታን የሚያስከብር አምልኮ

እውነተኛ የሆነ አገልግሎት

በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይሄ ነው (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ