ተናገር
Tenager
2013 · ትራክ 7 · 4:15 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እስከዛሬ ፊትህ ቀርቤ የልቤን ነግሬሃለሁ
እንዲሆንልኝ አስቤ ጠይቄሃለሁ
ፍላጐቴን በሙሉ አሰምቼሃለሁ
እስክትፈጽምልኝ ጐትጉቼሃለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
ዛሬ ግን በፊትህ ያለሁት ልናገር አይደለም
ምን እንደምትል ሃሳብህን ለማወቅ
ልሰማ መጥቻለሁኝ ተናገር
ዛሬስ የአንተ ጊዜ እንዲሆን አንተ እንድትናገር
ፈቃድህ ምን እንደሆነ እንድትገልጽልኝ
ምን እንዳደርግልህ እንደምትፈልግ
ስትናገር ልሰማ መጥቻለሁኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
ንገረኝ ምን እንዳደርግልህ ትወዳለህ
እንዴ እንድኖር ትፈልጋለህ
ልሰማ መጥቻለሁኝ ተናገር
አዝማች · Chorus
ተናገር (፫x) ልሰማ አለሁ ተናገር
ተናገር (፪x) እሰማሃለሁ ተናገር
ተናገር (፪x)
እሰማሃለሁ ተናገር
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ