ምንያህል በአንተ
Menyahel Bante
2013 · ትራክ 12 · 3:37 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ደግ ሰው መሆኔ የተነገረልኝ
በመልካም መግባሬ የተመሰገንኩኝ
እንዳልሆንኩ እያወቁ ወዳንተ አስጠጋኸኝ
ማንንነትህ ፍቅር ስለሆነ ወደደከኝ
አዝማች · Chorus
ምን ያህል በአንተ የተወደደኩ ነኝ ጌታ ሆይ
ምን ያህል በአንተ የተወደደኩ ነኝ
ፍቅርህ ማርኮኝ እኮ ነው የአንተ ያደረገኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
ዐይኖችህ ዘወትር ይመለከቱኛል
ጆሮዎችህ የልቤን ጪኸት ያደምጡኛል
በኑሮ ውጣ ውረድ መጓዝ ቢያቅተኝም
ተሸከምከኝ እንጂ ፈጽሞ አልተውከኝም
አዝማች · Chorus
ምን ያህል በአንተ የተወደደኩ ነኝ ጌታ ሆይ
ምን ያህል በአንተ የተወደደኩ ነኝ
ፍቅርህ ማርኮኝ እኮ ነው የአንተ ያደረገኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
በድካሜ አግዘኸኝ ጥፋቴን ሳትቆጥርብኝ
ከቁጣ ቀደመ ፍቅርህ ትወደኛለህ ደግ አባት ነህ (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ