Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ያልከው ይሆናል

Yalkew Yehonal

2013 · ትራክ 10 · 4:44 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ፈቃድህ ሆኖ ነው ትላንትን የኖርኩት

ፈተናን መጽናት ለማለፍ የቻልኩት

በራሴማ ቢሆን በገዛ ፍቃዴ

ትላንትን አልውልም እንኳን ልኖር ዛሬን

ምሥጋና አንተ ያልከው ይሆናል

እኔ ሰው ስለሆንኩ አይመስለኝም

ይሆናል አንተ ያልከው ምች ይቀራል

ሃሳብህ ሆኖ ነው አሁን የምኖረው

የማልፍበት መንገድ አንተ ያየኸው ነው

ስለእኔ ማታውቀው አንዳች ነገር የለም

ማስበው ማደርገው ከአንተ አልተሰወረም

እግዚአብሔር አንተ ያልከው ይሆናል

እኔ ሰው ስለሆንኩ አይመስለኝም

ይሆናል አንተ ያልከው ምች ይቀራል

ወደ ፊት ምኖረው ያልደረስኩበትን

ያልኖርኩበትን ቀን ገና ያላየሁትን

ተስፋ አለኝ እንድኖር ከአፍህ በወጣው ቃል

እኔ ያልኩት ሳይሆን ያልከው ይፈጸማል

እኔስ እንደራሴ/ስለራሴ ከማስበው ይልቅ

አንተ የተናገርከው የመሰከርክልኝ ትንቢት

ስለዚህ በደስታ ራሴን ሰጥሃለሁ

ትካዜዬን ሁሉ በአንተ ላይ ጥላለሁ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ