Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የዳዊት መሻት

Yedawit Meshat

2013 · 5:16 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ዓለምን ሁሉ አትርፌ ነፍሴን ግን በከንቱ ባጐድል

ለጊዜያዊ ነገር ብዬ እራሴን ስገኝ ስደልል

አልፈልግም እራሴን ማየት ለከንቱ ነገር ስንከራተት

እግዚአብሔር ሆይ ምለምንህ እንድኖር ብቻ ነው በፊትህ (፪x)

በፊትህ እንድኖር ብቻ ነው በፊትህ

ከዓለም እልፍ ቀን ይልቅ ከመኖር ከህልውና እሮሮ

አንድ ቀን ቤትህ ይሻላል መሸምገል ደግሞ እጅግ ይበልጣል

ግን አንድ ነገር እለምንሃለሁ እሷንም ደግሞ እጅግ እሻለሁ

በቤትህ ውስጥ ቀሪ ዘመኔን እያየሁ መኖር ነው ውበትህን

ውበትህን እያየሁ መኖር ነው ውበትህን ኦሆሆሆ

ውበትህን እያየሁ መኖር ነው ውበትህን

በውበት በዙፋንህ ላይ ሆሆሆ ስትስቅ ከሰማይ

አምልኮ ያስጨምረኛል ከዚህ በላይ ምን ያረካኛል

ከወደደከው ምን እላለሁ እይዘመርኩ መኖር ብቻ ነው

ደስ ካለህ ምን እላለሁ እየዘመርኩ መኖር ብቻ ነው

መሻቴ ጉጉቴ ይሄ ነው

አንተ ደስ ካለህ ደስ ካለህ

ምን እፈልጋለሁ ምን እፈልጋለሁ

ምን እላለሁ አመልክሃለሁ

ምን እላለሁ እያመለኩ መኖር ብቻ ነው

ደስ ካለህ ምን እላለሁ

እየዘመርኩ መኖር ብቻ ነው

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ