Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ዕውቀትህ ትልቅ ነው

Ewqeteh Teleq New

2013 · ትራክ 6 · 4:18 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሁልጊዜ ሳስበው ደስ የሚለኝ ነገር

የእኔ ሁለንተና ከአንተ አልመሰወር

መንገዴን ሃሳቤን ፍለጋዬን ሁሉ

መርምረህ አወቅህ ሕይወቴን በሙሉ (፪x)

ሰዎች ስለ እኔ ሚያውቁት የተወሰነ ነው

የሚናገሩት ሁሉ ሚያዩትን ብቻ ነው

. (1) . ከአንተ ጨለማ ይሰውረኛል ብል

ሌሊት በዙሪያዬ ብርሃን ይሆናል (፪x)

ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ

ከፊትህስ ርቄ የት እሸሻለሁ (፪x)

በሁሉ ቦታ ትኖራለህ

ዕውቀትህ ለእኔ እጅግ ትልቅ ነው

ልደርስበት የማልችል ከፍ ያለ ነው (፬x)

ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ

ከፊትህስ ርቄ የት እሸሻለሁ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ