Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሌት ይነጋል

Liet Yenegal

2013 · ትራክ 11 · 4:23 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ዕውቀት ስለአንተ ቢበዛ ደግ ነው

እምነት ያለስራ ግን ከንቱ ነው

እምነቴ ሲፈተን በመከራው ብዛት

ስጨነቅ በራሴ ሲውጠኝ ፍርሃት

ለመቼ ነው አምላክ አለኝ ማለቴ

አብሮኝ አለ ያልኩት ረዳቴ

ያገባሃል በእኔ ሕይወት እያልኩኝ

በራሴ ነገሬን ከጨረስኩኝ

በመልካም ቀን አምንሃለሁ ስልህ

በክፉ ቀን አለህ ሆይ ሳልልህ

እኔ እንዳልቀረሁ አንተ ታውቃለህ ጌታ

ቃሌ አምናለሁ በስራህ . (1) .

አምንሃለሁ ቃሌ አይበጀኝም

የቃሌ ብዛት እኔን አልሰራኝም???. (2) .

ተግባሩ እንጂ ቢበዛም ሳንኮፉ???. (3) .

ከጌታ ጋር ሁሉን እያለፉ

ሌት ይነጋል ሠማዩም ይጠራል

የታመነ ከእርሱ ጋራ ያርፋል

ሌት ይነጋል ሠማዩም ይጠራል

የታመነ ከእርሱ ጋራ ያድራል (፪x)

ከእርሱ ጋራ ያድራል

ከእርሱ ጋር ያርፋል የታመነ

የሠማይ ወፎች አይዘሩም አያጭዱም

ለነገም አስበው ከጐተራም አይከቱም

እነሱን ያተገብክ አንተ ደግ አባት ነህ

እኔማ ልጅህ ነኝ ምልህ ትሆናለህ

ለመቼ ነው አምላክ አለኝ ማለቴ

አብሮኝ አለ ያልኩት ረዳቴ

ያገባሃል በእኔ ሕይወት እያልኩኝ

በራሴ ነገሬን ከጨረስኩኝ

ሌት ይነጋል ሠማዩም ይጠራል

የታመነ ከእርሱ ጋራ ያርፋል

ሌት ይነጋል ሠማዩም ይጠራል

የታመነ ከእርሱ ጋራ ያልፋል

ሌት ይነጋል ሠማዩም ይጠራል

የታመነ ከእርሱ ጋራ ያድራል (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ