Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አንተን እባርክሃለሁ

Anten Ebarkehalehu

2013 · ትራክ 3 · 4:51 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አሁን ከገጠመኝ ፈተና በስተጀርባ

ድል እንዳለ አውቃለሁ ሚሆን ከአንተ ጌታ

ስለዚህ ይህንን መከራ ሳስበው

ከኋላ ያለውን ድል ለማየት እጓጓለሁ

ከልቤ አንተን እባርክሃለሁ

ወድጄ ለአንተ እገዛልሃለሁ (፪x)

የማማርርበት ምክንያት አንድ የለኝም

ለገጠመኝ ችግር አላጉረመርምም

ለምን ቢባል ሁሉም በጐ ታደርጋለህ

ለመልካም ለውጠህ ታስደንቀኛለህ

ከልቤ አንተን እባርክሃለሁ

ወድጄ ለአንተ እገዛልሃለሁ (፪x)

ስለምትሰማኝ እነግርሃለሁ (እነግርሃለሁ)

ስለምትረዳኝ እታመንሃለሁ (እታመንሃለሁ)

ስለምትይዘኝ (ስለምትይዘኝ) እደገፍሃለሁ

ሆሆሆሆ ሆሆሆ አመሰግናለሁ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ