የኢየሱስ ደም
YeEyesus Dem
2013 · ትራክ 1 · 5:20 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የኃጢአቴ መብዛት ጐልቶ ይታየኛል
እርሱን መበደሌ በደምብ ታውቆኛል
ይህንን በሙሉ ሳስበው ብፈራም
ኃጢአቴ የበረታ መስሎ ቢሰማኝም
አዝማች · Chorus
የኢየሱስ ደም ለእኔ የፈሰሰው
አንዳች ሳያስቀር በደሌን አጠበው
የኃጢአት ፍርሃት ከእኔ ተወግዷል
በደሙ ያለው ኃይል ነጻ አውጥቶኛል
ቁጥር 2 · Verse 2
ኃጢአተኛ እንደሆንኩ እግዚአብሔርም ያውቃል
ለዚህም እንዲሆን ልጁን ልኮልኛል
ከኃቲአቴ እና ከበደሌ ኃይል
የክርስቶስ ደም ጉልበት እጅግ ይበረታል
አዝማች · Chorus
የኢየሱስ ደም ለእኔ የፈሰሰው
አንዳች ሳያስቀር በደሌን አጠበው
የኃጢአት ፍርሃት ከእኔ ተወግዷል
በደሙ ያለው ኃይል ነጻ አውጥቶኛል
ቁጥር 3 · Verse 3
ነጻ ነጻ አውጥቶኛል ኦሆሆ
እኔን ሲታደገኝ ከዘለዓለም ሞት
ጐሳና ቀለሜን እርሱን መቼ አግቶት
ዘሬና ቋንቋዬ ምንም ቢሆን ምንም
ደሙ እኔን ለማዳን ፈጽሞ አልደከመም
አዝማች · Chorus
የኢየሱስ ደም ለእኔ የፈሰሰው
አንዳች ሳያስቀር በደሌን አጠበው
የኃጢአት ፍርሃት ከእኔ ተወግዷል
በደሙ ያለው ኃይል ነጻ አውጥቶኛል
ቁጥር 4 · Verse 4
የኢየሱስ ደሙ ብርቱ ነው
ኃይል አለው ጉልበት አለው
ኃጢአቴን አጠበው (፫x)
አጠበው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ