Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አምላኬ ፍቅር ነው

Amlakie Feqer New

2013 · ትራክ 4 · 3:59 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ለክብሩ ሳይገደው ከሠማይ ወረደ

እኔኑን ለማዳን ራሱን ዝቅ አደረገ

እንዲህ እንዲወደኝ ነፍሱን እንዲሰጠኝ

ከእኔ መልካም ነገር ፈጽሞ አልተገኘም

ለሰላሙ. (1) . ሃጥያት የተፈረደብኝ

የዘለዓለም ሞት ነበር የሚገባኝ

አላስችል ስላለው ለእኔ ያለው ፍቅር

መሰቀል መረጠ ከአባቱ ክብር

አስደናቂ ፍቅሩን ለእኔ የገለጠው

አምላኬ ፍቅር ነው (፬x)

የእኔን ሞት ሞቶ ሕይወትን ሰጥቶኛል

እርሱ ተሰቃይቶ በፍቅር ወልዶኛል

ደህንነት አግኝቼ በደስታ ምኖረው

ያቆመኝ በሕይወት የጌታ ፍቅር ነው

አምላኬ ፍቅር ነው

አምላኬ ፍቅር ነው

አምላኬ ፍቅር ነው

ኦሆሆ ፍቅር ነው (፭x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ