ፍቅርህ ነው
Feqereh New
2013 · ትራክ 9 · 4:49 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የመዳኔ ምክንያት ምህረት የማግኘቴ
አንተ ነህ እንጂ ምን አለ ከእኔ
ይህ ስለገባኝ አመሰግናለሁ
እውነተኛ ወዳጅ ለአንተ እዘምራለሁ
ነፍስህን እስከመስጠት ድረስ ወደኸኛል ጌታዬ
ለእኔ ለኀጢአተኛው በመስቀል ሞተሃል ጌታዬ (፪x)
አዝማች · Chorus
አምላኬ ሄሄ ኦ ሁልጊዜ አመሰግናለሁ
ኦኦኦኦ ሁልጊዜ ለአንተ እዘምርልሃለሁ
ኦ ሁልጊዜ አመሰግናለሁ
ኦኦኦኦ ሁልጊዜ ለአንተ እዘምርልሃለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
አይደለም እንደኔ እንደኀጢአቴ ብዛት
አምላክ ያሳየኸኝ የምህረትህን ስፋት
እንዲሁ በጸጋህ ፍቅርህ አድኖኛል
ለመውደድህ ምላሽ ከቶ የት ይገኛል
እግሮቼን ከጥፋት መልሰሃልና ጌታዬ
ሳጸለች በፍቅር ይዘኸኛልና ጌታዬ
እግዚአብሔር ከጥፋት መልሰሃልና ጌታዬ
ሳጸለች በፍቅር ይዘኸኛልና ጌታዬ
አዝማች · Chorus
አምላኬ ሄሄ ኦ ሁልጊዜ አመሰግናለሁ
ኦኦኦኦ ሁልጊዜ ለአንተ እዘምርልሃለሁ
ኦ ሁልጊዜ አመሰግናለሁ
ኦኦኦኦ ሁልጊዜ ለአንተ እዘምርልሃለሁ
ቁጥር 3 · Verse 3
ፍቅርህ ነው (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የማረኝ ያዳነኝ ፍቅርህ ነው ፍቅርህ ነው
አዲስ ሰው ያረገኝ ፍቅርህ ነው ፍቅርህ ነው
የማረኝ ያዳነኝ ፍቅርህ ነው ፍቅርህ ነው
ሕይወትን የሰጠኝ ፍቅርህ ነው ፍቅርህ ነው (፪x)
ፍቅርህ ነው (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ