Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አንድ ነን

And Nen

2026 · ትራክ 8 · 3:52 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የማንቀራረብ የማንቀላቀል

የማንፈላለግ የምንኖር በጥል

በነገድ በቋንቋ ልዩ ልዩ የነበርን

ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ አቃረበን

አሁን ወንድም እና እህቶች ተብለን

በአንድ መንግስት ውስጥ አብረን እንኖራለን

አንድ አካል የሆነ የቅዱሳን ህብረት

ተሰጥቶናል ሰላም ሆኖልናል ጥምረት

ከእንግዲህ አይሁድ የለም ወይም የግሪክ ሰው

ባሪያ ነው የሚባል ወይንም ነፃ ነው

በኢየሱስ አምነን ዳግም የተወለድን

ሁላችን በአንድነት የአግዚአብሄር ህዝቦች ነን

አንድ ነን በጌታ

አንድ ነን በኢየሱስ

ክርስቶስ የፀና መሰረት ሆነልን

እንገነባለን እየተናነጽን

ክፉ ምን ቢተጋ ችሎ የማያፈርሰው

በክርስቶስ የሆነ ህብረታችንን ነው

አንድ ነን በጌታ

አንድ ነን በኢየሱስ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ