የእግዚአብሄር ልጅ
Ye'egziabher Lij
2026 · 5:16 · አማርኛ
ክርስቶስ የህያው የእግዚአብሄር ልጅ ነህ
ይህንን አምኜ እኔም ተከተልኩህ
ብዙዎች በስህተት መንገድ ይገልጡሃል ይረዱሀል (ይገልጡሀል)
አንዳንዶች እንዲያውም ኤሊያስ ይሉሃል
ሌሎችም ከነብያት ከአንዱ ይመድቡሃል
እኔ ግን አንድ እውነት ህይወት በርቶልኛል
የሰው ልጅ በሀጥያት ታሞ ለዘመናት
አብ ለአለም የሰጠህ አንተ ነህ መድሀኒት
የምወደው ልጄ እርሱን ስሙት ያለው
ኢየሱስ ክርስቶስ አዎ አንተን ብቻ ነው
አዝማች · Chorus
አምናለሁ ከአብ እንደመጣህ
ብቸኛ መዳኛ እንደሆንህ
በአንተ ካልሆነ በስተቀር
አይቀርብም ማንም ወደ እግዚአብሄር
በአንተ ብቻ 2x
በአንተ ነው አለም የሚድነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ