አባት አለኝ
Abat Alegn
2026 · ትራክ 1 · 4:05 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አባ ብዬ እንድጠራው ያደረገኝ
ልጄ ብሎ የሚጠራኝ የሚወደኝ
እርሱ አለልኝ የምለው የማሳየው
የሰማዩ አባቴ እግዚአብሄር ነው
መኖሪያዬን አድርጎት ቤቱ
መውጣት መግባቴ ነው በፊቱ
በእረፍት ውሀ ዘንድ ይመራኛል
ገበታን ያዘጋጅልኛል
በሞት ጥላ እንኳን መካከል ብሄድ
እርሱ ከእኔጋ አለ ልቤ አይርድ
ስጋት የሌለው ህይወት ሰጥቶኛል
በአባትነቱ አስተማምኖኛል
አዝማች · Chorus
አለኝ አለኝ አለኝ አባት አለኝ
አለኝ አለኝ አለኝ የሚያኖረኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
አባት ነለኝ የሚያኖረኝ
አባት አለኝ የሚያኖረኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
ጎደለኝ አልል እርሱ እያለኝ
የሚያስፈልገኝን የሚያደርግልኝ
ለእንሰሶች ለእጽዋት ካሰበ
ለእኔ ያደርጋል የበለጠ
ከቶ አልጨነቅ በማየው ነገር
ከምስጋናጋ ከመንገር በቀር
በሀይሉ ችሎት እታመናለሁ
አባቴ የለም አንድም የሚሳነው
አዝማች · Chorus
አለኝ አለኝ አለኝ አባት አለኝ
አለኝ አለኝ አለኝ የሚያኖረኝ
ቁጥር 4 · Verse 4
አባት አለኝ የሚያኖረኝ
አባት አለኝ የሚያኖረኝ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ