ለእኔ ህይወት
Le'ene Hiwot
2026 · 3:48 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ለእኔ ህይወት ክርስቶስ ነው
ሞትም ለጥቅም ሆኖልኛል
ከአዳነኝ ከአንዱ ጌታዬ
እስኪ ማን ችሎ ይለየኛል
ሀጥያተኛ ነበርኩ በእርሱ ላይ ያመጽኩኝ
እንደስጋ ምኞት ስመላለስ ምገኝ
በበደሌ ምክንያት ሙት ለነበርኩት
ኢየሱስ እኮ ነው የሰጠኝ ህይወት
በእኔ ፈንታ ሊሞት እራሱን እስኪሰጥ
የገለጠው ፍቅሩን በልቤ አፍስሶት
አዝማች · Chorus
አልችልም ከኢየሱስ መለየት
ቁጥር 2 · Verse 2
ኑሮ ማለት ለእኔ ነው ከኢየሱስ ጋራ
ቁጥር 3 · Verse 3
በፍቅሩ እጸናለሁ ባልፍም በመከራ
እስከመጨረሻው እከተለዋለሁ
በዚህ ሁሉ አቅሜ ብርታቴ ጸጋው ነው
ከምድር ባለፈ የዘለአለም ህይወት
እንዲኖረኝ ተስፋን ከተቀበልኩበት
አዝማች · Chorus
አልችልም ከኢየሱስ መለየት
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ