Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ደጋግሜ

Degagme

2026 · ትራክ 2 · 5:48 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ለወደድከኝ ከሀጥያቴም በደምህ ላጠብከኝ

ለአባትና ለአምላክህ ካህን እንድሆን ላረከኝ

ላንተ ክብር ይሁን

ከእግዚአብሄር ርቄ በሀጥያት

አቅም ሳጣ የምላቀቅበት

ኢየሱስ በአንተ ቤዛነት ሆኖልኝ

ከዘለአለም ሞት አመለጥኩኝ

በፈሰሰው ደምህ አጥበኸኛልና

አንጽተህ ቀድሰህ ቀርቤያለሁና

ክበር እላለሁ እንደገና

ፊትህ እሆናለው ለምስጋና

ክበር እላለሁ ደጋግሜ

በምህረትህ ተገርሜ

በአንተ ይቅርታ ተገርሜ

በጨለማ የምመላለስ ሳለሁ1

ወደብርሀን መጠራት አገኘሁ

ለህይወቴ ደርሰህ በማዳንህ

በርቶልኛል የእውነት መንገድህ

ከቅዱሳን ጋራ ቆጥረኸኛልና

ህያው ተስፋን በአንተ አጊንቻለሁና

ክበር እላለሁ እንደገና

ፊትህ ቆማለሁ ለምስጋና

ክበር እላለሁ ደጋግሜ

በምህረትህ ተገርሜ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ