አዲሱ መንገድ
Adisu Menged
2026 · ትራክ 10 · 3:19 · አማርኛ
የሰውን ልጅ ደካማነት
እግዚአብሔር በመመልከት
አዲስ መንገድ ከፍቷል የሚዳንበት
ታላቅ የምስራች ለአለም ሁሉ የሚሆን
ከአምላክ ጋር ታረቁ በልጁ በማመን
እግዚአብሄር ቃል ስጋ ሆነ ለሁሉ አንዴ ለመሞት
በመስቀል ባፈሰሰው ደም ሊያነጻ የአለምን ሀጥያት
በሞትና በትንሳኤው በማዳኑም የሚያምኑ ሁሉ
በእርሱ በሆነው ቤዛነት እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ
የአለምን ሁሉ ሃጥያት የሚያስወግድ የሚያድነው
ከእግዚአብሄር አብም የሚያደርሰው
አዲሱ መንገድ ኢየሱስ ነው
አዲሱ መንገድ ኢየሱስ ነው
አዲሱ ህይወት ኢየሱስ ነው
አዝማች · Chorus
ከእግዚአብሄር ጋር ለመስማማት በልቡ የሚሻ ካለ
ሀጥያትም ከባድ ሸክም ሆኖበት የተቸገረ
ከታላቁም የአምላክ ቁጣ ለማምለጥ የሚወድ ቢኖር
ወደ ኢየሱስ ፈጥኖ ይምጣ ወደሆነው የድነት በር
የአለምን ሁሉ ሃጥያት የሚያስወግድ የሚያድነው
ከእግዚአብሄር አብም የሚያደርሰው
አዲሱ መንገድ ኢየሱስ ነው
አዲሱ መንገድ ኢየሱስ ነው
አዲሱ ህይወት ኢየሱስ ነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ