Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ስላልፈቀድክልኝ አመሰግናለሁ

Slalfekedkilign Ameseginalehu

2026 · ትራክ 7 · 4:44 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ለእኔ የምታስበው እግዚአብሄር መልካም ነው

ለክፉ እንዳትተወኝ ይህን አውቂያለሁ

ከእኔ ሀሳብ ይልቅ የአንተን እያፀናህ

ዛሬ የምደርስበት መንገዴን አቀናህ

ስለሆነ አንተ ያልከው

እጅግ ብዙ አትርፊያለሁ

አቆየኸኝ በጥበቃህ

አዘለቅኸኝ በምህረትህ

የለመንኳቸውን ሁሉ አልሰጠኸኝም

ለገዛ ፈቃዴ ፈጽሞ አልተውከኝም

መጥቶ የሚረባኝን ብቻ እያደረግህ

ከፊትህ አልጠፋሁም ብዙ ነው ማዳንህ

መከልከል በጊዜው ደስ ባያሰኝም

በጉዳት ከሚፈስ እንባ ግን አይበልጥም

ለበጎ ሆኖልኛል ዛሬ ላይ ሳስበው

ስላልፈቀድክልኝ አመሰግናለሁ

በሰው አይን ሲታይ እድል ከሚመስል

በአጅ የገባ እለት ግን ብዙ ከሚያጎድል

ረብ ከሌለው ነገር በመንገዴ ቆመህ

ከስንቱ ያስመለጥከኝ አምላኬ አንተ ነህ

መከልከል በጊዜው ደስ ባያሰኝም

በጉዳት ከሚፈስ እንባ ግን አይበልጥም

ለበጎ ሆኖልኛል ዛሬ ላይ ሳስበው

ስላልፈቀድክልኝ አመሰግናለሁ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ