Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ልቀህ ታይ

Likeh Tay

2026 · ትራክ 3 · 5:48 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በምህረትህ ምኖር በምህረትህ ድኜ

የጸጋህ ጥገኛ ተደጋፊ ሆኜ

በድካሜ ሀይልህ እንዲታይ ልትሰራብኝ ወደሀል

እኔም ደግሞ በመገዛት ላከብርህ ይገባኛል

በእኔ በሸክላዋ ከሁሉ በማንሰው

የከበረን መዝገብ በውስጤ ያኖርከው

ስምህን የሚሸከም እቃ ያደረከኝ

ባለቤቴ አንተ ነህ ወደህ ምትሰራብኝ

እኔ ዝቅ ልበል አንተ ክበርልኝ

እንዳገለግልህ ካህን ያደረከኝ

የመንግስትህ ወንጌል ካህን ያደረከኝ

ሊቀ ካህናት ልቀህ ታዪ ልቀህ ታዪ 4x

ኢየሱስዬ

መድኋኒያለም

ደምቀህ

አንተ ጌታዬ ነህ እኔ ደግሞ ሎሌህ

በራሴ አንዳች የለኝ አቅሜም እንተው ነህ

ታማኝ አርገህ ቆጥረህ በእኔ ላይ ስትሰራ

ትምክህት የለኝም ጌታ ካንተ ሌላ

አንተ ደምቀህ ታይ

ኢየሱስ ከብረህ ታይ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ