Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ነፍሴ ታከብርሀለች

Nefse Takebirhalech

2026 · ትራክ 5 · 5:13 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እንደ ቻልኩኝ ሆነህ ጉልበቴ

የቆምኩብህ የጸና ዓለቴ

የሚያየኝ ይወቅ እንደሆንክ ረዳት

እንደበዛልኝ የአንተ በጎነት

በህይወቴ ስለሆነው እያንዳንዱ ነገር

አምላኬ አንተ ብቻ ክብርን ተቀበል*2

በህይወቴ ስለሆነው እያንዳንዱ ነገር

አምላኬ አንተ ብቻ ክብርን ተቀበል*2

ስንቴ ምርኩዝ ሆንከኝ የምደግፍበት

ከድካም ዝለቴ የማንሰራበት

ሁሉን ከምትችለው ኃይልን ተቀብዬ

ያላለፍኩት የለም አቤቱ ጌታዬ

ሁሉን ከምትችለው ኃይልን ተቀብዬ

ያላለፍኩት የለም አቤቱ ጌታዬ

ክበር ክበር ነፍሴ ታከብርሃለች

ብዙ ማዳን ምህረትህን ስላየች

ክበር ክበር ነፍሴ ታከብርሃለች

በአንተ ብዙ በጎነትን ስላየች

ክበር ክበር ነፍሴ ታከብርሃለች

የማይነጥፈው ምህረትህን ስላየች

ክበር ክበር ነፍሴ ታከብርሃለች

በአንተ ብዙ ርህራሄን ስላየች

የመከራዬና የጭንቀቴን ጩኸት

ሰምተህ መልሰሃል ሆነኸኛል እረፍት

አምነው ለሚጠሩህ እንደማታሳፍር

ለደራሽነትህ እኔ አለው ምስክር

አምነው ለሚጠሩ እንደማታሳፍር

ለደራሽነትህ እኔ አለው ምስክር

ክበር ክበር ነፍሴ ታከብርሃለች

ብዙ ማዳን ምህረትህን ስላየች

ክበር ክበር ነፍሴ ታከብርሃለች

በአንተ ብዙ በጎነትን ስላየች

ክበር ክበር ነፍሴ ታከብርሃለች

የማይነጥፈው ምህረትህን ስላየች

ክበር ክበር ነፍሴ ታከብርሃለች

በአንተ ብዙ ርህራሄን ስላየች

ምህረትህን ስላያች ምህረትን ስላየች

በጎነትህን ስላያች በጎነትህን ስላየች

ምህረትህን ስላየች ምህረትን ስላየች

ርህራሄህን ስላየች ርህራሄህን ስላየች

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ