Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ማራናታ

Maranatha

2026 · ትራክ 9 · 5:39 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አንድ ደስታ አለን ውስጣችን የሞላን

ፈተና ቢበዛም ሁሌ የሚያጽናናን 2x

የዚች አለም ክፋት ቢያሰለቸንም

የተሰጠን ተስፋ ሚታጠፍ አይደለም

ኢየሱስ ይመጣል ደግሞም አይዘገይም

ናፍቆታችን እርሱን ያዳነንን ጌታ

ሁሌ እንለዋለን አሜን ማራናታ

እርሱ የሚኖርበት እኛም እንድንኖር

የተስፋን ቃል አለን መቶ እንደሚወስደን

ሰዎች እንዲድኑ ይታገሳል እንጂ

ቃሉን ይጠብቃል የእግዚአብሄር ልጅ

እኛስ አለን ተስፋ አዎ

የማይሻር የማይጠፋ አዎ

እኛስ አለን ርስት አዎ

ሁሉም አልፎ ምናርፍበት አዎ

በክርስቶስ የሞቱት ቀድመው ይነሳሉ

በህይወት የሚኖሩት ደግሞ ይነጠቃሉ

የሚለውን ቃሉን እንድናይ ሲፈጸም

ጽኑ ነው ልባችን አንጠራጠርም

እኛስ አለን ተስፋ አዎ

የማይሻር የማይጠፋ አዎ

እኛስ አለን ርስት አዎ

ሁሉም አልፎ ምናርፍበት አዎ

ማራናታ ኢየሱስ ሆይ ና

እንላለን ናፍቀናልና

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ