እስቲ ወደማን
Esti Wedeman
2026 · ትራክ 4 · 5:30 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የማዳንህ እውነት ሳያጠራጥረን
ወደ ግራ ወደቀኝ አማራጭ ሳያምረን
ኢየሱስ ሆይ አንተን እንከተላለን
ከላይ ከሰማያት የወረድህ መና
የነፍስን ረሀብ ጉድለት የምትሞላ
የህይወት እንጀራ ኢየሱስ አንተ ነህ
ዘለአለም ይኖራል ባንተ ያመነብህ
አዝማች · Chorus
ጌታ ሆይ ካንተ ወደማን እንሄዳለን
ከቶ ወደማን እንሄዳለን
ጌታ ሆይ ካንተ ወደማን እንሄዳለን
እስቲ ወደማን እንሄዳለን
አውቀናል ደግሞም አምነናል ያላንተ የለም የሚያድን
ቁጥር 2 · Verse 2
አናፈገፍገም ከሰማነው ቃልህ
ከባርነት ቀንበር ካወጣን ከፍቅርህ
በአንተ እንኖራለን በእምነት በመጽናት
ለሁለንተናችን ሆነከናል ሙላት
አዝማች · Chorus
ጌታ ሆይ ካንተ ወደማን እንሄዳለን
ከቶ ወደማን እንሄዳለን
ጌታ ሆይ ካንተ ወደማን እንሄዳለን
እስቲ ወደማን እንሄዳለን
አውቀናል ደግሞም አምነናል ያላንተ የለም የሚያድን
ቁጥር 3 · Verse 3
ሁሉን ትተን ተከትለንሃልበ 2x
የጣልነውን ዳግም አናነሳም
የያዝነውን እውነት አንረሳም
አብ ስቦናል እንድንከተልህ
ኢየሱስ ሆይ ዘለአለም ጌታ ነህ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ