Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በቸርነቱ

Bechernetu

2026 · ትራክ 11 · 5:01 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በቸርነቱ

መልካሙም ሆነ ክፉውም ሆነ

ሀዘኑም ሆነ ደስታውም ሆነ

በዚህ ሁሉ ግን ጌታ አስችሎን

ዳግም ቆመናል ለክብሩ እንድንሆን

አማኑኤል ከእኛ ጋራ ሆኖልናል እንዳንፈራ

ያንን ሁሉ ያሻገረን የምስጋና መዝሙር ሆነን

የእኛ ችሎታ የቱ ነው የቱስ አቅማችን

ዋስትና የሚሆን እስካሁን ስለመኖራችን

አንድም ተጨንቆ ቁመቱን ያረዘመ የለም

እንደ ፈቃዱ በፊቱ ይኖራል ሁሉም

በቸርነቱ ዘመናት ለሚያቀዳጀው

ለእግዚአብሄር ክብር ይሁን ሀሌሉያ

ልመናችንን አልናቀ ጮኸን ስንጣራ

ህይወታችንን አዳናት ከጥፋት ጎዳና

ለጠላት ደስታ አልሰጠን እጁ አሳልፎ

ብርቱ አደረረገን በመልካም ክንዱ ደግፎ

በእኛ ላይ የእግዚአብሔር ማዳን ገነነ

ገነነ ጥበቃው

ገነነ ምህረቱ

ገነነ ማዳኑ

ገነነ ብርታቱ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ