አንቃኝ
Anqagn
2014 · ትራክ 7 · 6:47 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከአንተ ጋራ ኖሬ አንተን አስከብሬ ፍሬን እንዳፈራ
ነበረ ምኞትህ ያሁሉ ልፋትህ እኔን ስትሰራ
ቅጠሉ እንዳማረ ግን ፍሬ እንደሌለው በለስ ሆኛለሁ
ጥቂት ታገሰኝ አንድ እድል ስጠኝ ፊትህ ወድቄያለሁ
አዝማች · Chorus
እንዳትተወኝ እማጸናለሁ
ከተውከኝማ ወዴት እሄዳለሁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ባጠፋ እንኳ ቆንጥጠህ መልሰኝ
ብበድልህ እንኳ ገስጸህ መልሰኝ
የእኔ ጌታ ያለአንተ ማን አለኝ
አዝማች · Chorus
ድንጋዩን ልቤን ባክህ አውጣልኝ አባ እባክህ አውጣልኝ
አዲስን መንፈስ በውስጤ አኑርልኝ ጌታ በውስጤ አኑርልኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
ድምጽህን ስሰማ አው አልሁን እልኸኛ
ቸል ብዬ እንዳልጠፋ አባ እባክህ አንቃኛ
አዝማች · Chorus
እባክህ አንቃኛ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የሰጠኸኝን ያንን አደራ ያንን መክሊት
ነበር ነቅቼ እንድጠብቅህ ብዙ አትርፌበት
ምንም ሳልሰራ እንደቀበርኩት ምጻትህ ቀርቧል
አንቃኝ ጌታዬ ከስንፍናዬ ኋላ እንዳልጣል
አዝማች · Chorus
ዝም እንዳትለኝ እማጸናለሁ
ዝም ካልክማ እኔ እፈራለሁ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
አባ አድነኝ ከቁጣህ አድነኝ
አድነኝ ኢየሱስ አድነኝ
ለጠፊው ዓለም ስጥር ስለፋ ጊዜዬ አልቆ
ሠማያዊውን የዘለዓለሙን ልቤ ዘንግቶ
ኃይሌ ተሟጦ ዘይቴ አልቆ ባዶ ሆኛለሁ
ማረኝ አባቴ ገባኝ ጥፋቴ እመለሳለሁ
አዝማች · Chorus
እኔን ለምኞቴ አትስጠኝ ጌታዬ አትስጠኝ ጌታዬ
እኔን ለሥጋዬ አትስጠኝ አባዬ አጽጠኝ አባዬ
ቁጥር 6 · Verse 6
እግዚአብሔርን መፍራት ጠፍቶ የለም ወይ
ምኞቱን የሚያረግ ሞልቶ የለም ወይ
ባክህ በዚህ ዘመን አባ አስተዋይ አድርገኝ
ወደ ጽድቅ ጐዳና አሃ እግሬን መልስልኝ
አዝማች · Chorus
አድነኝ አባ አድነኝ ኢየሱስ
አድነኝ ጌታ አድነኝ አን..
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ