አትለፈኝ
Atelefegn
2014 · ትራክ 2 · 6:24 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከአንተ ወደ ማን እሄዳለሁ ማን አላት ነፍሴ
ለሕይወቴ ትርጉም አንተ አይደለህ ወይ ክብሬ ሞገሴ
ያለአንተ እንዴት እኖራለሁ እንዴት እሆናለሁ
ከውኃ እንደወጣ ዓሣ ያኔ እጠፋለሁ
አዝማች · Chorus
ከአንተ ጋራ መኖር ይሻለኛል
ሕይወቴ ነህ አልፈልግም ላጣህ አንተን
ከአንተ ጋራ መኖር ይሻለኛል
ሰላሜ ነህ አልፈልግም ላጣህ አንተን
ዋናዬ ነህ ዋናዪ ነህ እኔስ አልጣህ
ዋናዬ ነህ ዋናዬ ነህ እኔስ አልጣህ
ቁጥር 2 · Verse 2
በሰፈሬ በመንደሬ ድል ልትሰጠን ስትመጣ
ጉብኝትህ እንዳያልፈኝ በስፍራዬ እንዳልታጣ
ጠብቅሃለሁ ተሰናድቼ ቤቴን መንደሬን አጸዳድቼ
ጠብቅሃለሁ ተሰናድቼ ቤቴን መንገዴን አጸዳድቼ
ጠብቅሃለሁ ጌታ ተሰናድቼ
ቤቴን ጓዳዬን አሃ አጽዳድቼ (፪x)
አዝማች · Chorus
አምላኬ ፊትህን እሻለሁ በዚህ ቦታ
እንድትዳስሰኝ ለአንድ አፍታ
አትለፈኝ ጌታ አትለፈኝ ጌታ
አትለፈኝ ኦሆ አትለፈኝ ኦሃ
አትለፈኝ አባ አትለፈኝ ኦሆ
ጌታ ጌታ አትለፈኝ አትለፈኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
ጸሎቴ ጩሄቴ ሞገስ ያግኝህ ሞገስ ያግኝህ
አትለፈኝ አትለፈኝ ያለ አንተ ሕይወት ሕይወት የለኝም
አትተወኝ አትተወኝ ያለአንተ ኑሮ አይሆንልኝም አዎ
ልቤ እያወቀው መውደቅ መሸነፌን
የግብዝነቴ ታገለው መንፈሴ
አስመስሎ መኖር በቃ ይበቃኛል
ለውጠኝ አባቴ ሕይወት ይሻለኛል
ይሻለኛል ሕይወት ይሻለኛል (፪x)
አዝማች · Chorus
አትለፈኝ ኦሆ አትለፈኝ ኦሆ
ሽንገላ ተሞልቶ አቤት አንደበቴ
ጉልበቴን ጨረስኩት ባዶ ሆነ ቤቴ
ያው ከነድካሜ ፊትህ ወድቄያለሁ
ለፈቃዴ አትስጠኝ እለመንሃለሁ
ሁሉን ልጣ አንተን ከማጣ አባ አንተን ከማጣ
ሁሉ ይቅር አንተ ከምትቀር አባ አንተ ከምትቀር (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
አንተው ትሻለኛለህ
አንተው ትበቃኛለህ
ነፍሴን ለአንተ ሰጥቻለሁ
አባ ተማርኬያለሁ
ተማርኬያለሁ ተማርኬያለሁ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ