ማን ትሉታላችሁ
Man Telutalachehu
2014 · ትራክ 5 · 4:49 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ኢየሱስን ማን ትሉታላቹህ
ከማንስ ጋር ታስተያዩታላቹህ
የእኔን ጌታ ማን ትሉታላቹህ
ከየትኛው ታስተያዩታላቹህ
እርሱ እኮ ነው ሞትን የረታ
ማኅተሙን ብቻውን የፈታ
አዝማች · Chorus
የጌቶቹ ጌታ የጌቶቹ ጌታ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ብዙዎች ነበሩ ኃያል ነን ያሉ
ዘመን ሲቀየር እነርሱ ግን የሉ
እንዲያው በነበር ቀረ ዝናቸው
መቃብር አሉ ሞት ድል ነስቷቸው
ሞተ አበቃ አከተመለት
እያለ ሰይጣን ሲሳለቅበት
ሞት መቼ ያዘው ይህን አንበሳ
በሶስተኛው ቀን ኢየሱስ ተነሳ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ተነሳ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ፍጥረት ይህን ይስማ ይታወቅ እውነቱ
ሞትን ድል ያረገ እስኪ ማነው ብርቱ
መጽሃፉን ከፍቶ ማኅተሙን የፈታ
ኢየሱስ ብቻ ነው አሸናፊ ጌታ
አዝማች · Chorus
አሸናፊ ጌታ (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እንደ ጋለ ነሃስ አቤት እግሮቹ
እንዴሳት ነበርላብ ናቸው ዐይኖቹ
ደረቱን በወርቅ መታጠቂያ ታጥቆ
አለ ይኖራል ዘለዓለም ደምቆ
ፊቱ ከፀሐይ በላይ ያበራል
ግርማ ሞገሱ እጅግ ያስፈራል
ይሄ ነው ጌታ እኔ የማመልከው
ሰምቶ በእሳት የሚመልሰው
አዝማች · Chorus
የሚመልሰው (፬x)
ጌታ ነው አቻ የሌለው (፬x)
አቻ የሌለው (፬x)
ቁጥር 5 · Verse 5
በሠማይ በምድር ከምድርም በታች
መቼ ተገኘ መጽሃፉን ከፋች
ዮሐንስ ሲያለቅስ ይህንን አይቶ
አታልቅስ አለው መላዕኩ መጥቶ
መጽሃፉን ሊከፍት ማኅተሙን ሊፈታ
ጀግና ተገኝቷል የጌቶች ጌታ
ከዳዊት ዘር ግንድ ያቆጠቆጠው
የይሁዳ አንበሳ ሁሉን ፈታታው
አዝማች · Chorus
ሁሉን ፈታታው (፬x)
ጌታ ነው አቻ የሌለው (፬x)
አቻ የሌለው (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ