ያኖረኛል
Yanoregnal
2014 · ትራክ 3 · 5:23 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ምሥጋና የተጋውን እግዚአብሔርን እጠራዋለሁኝ
መቅደሱን በዕልልታዪ እበዝማሬ እሞላዋለሁ
ይኸው ምሥጋናው ይኸው ዝማሬው
ይኸው ዕልልታው ስለሚገባው (፪x)
የሚሰዋልኝ ለእኔ ምሥጋና
እርሱ ያከብረኛል ብሎኛልና
ሞላ ጐደለ ሳልል እሰዋለሁ
በሙሉ ኃይሌ አመልከዋለሁ
አመልከዋለሁ (፬x)
ነገ ለራሱ ይጨነቅ ይጨነቅ እንጂ
እኔስ አርፌ እኖራለሁ በአምላኬ እጅ
ነገ ለራሱ ይጨነቅ ይጨነቅ እንጂ
እኔስ አርፌ እኖራለሁ በአምላኬ እጅ
አዝማች · Chorus
ነገሬን በሚያውቅልኝ በእርሱ ላይ እጥላለሁ
ትላንትን ያሻገረኝ ለነገም አምነዋለሁ (፪x)
ያኖረኛል እርሱ ያሳየኛል
ያኖረኛል እርሱ ያሳየኛል
ያኖረኛል ገና ያሳየኛል
ያኖረኛል እርሱ ያሳየኛል
ቁጥር 2 · Verse 2
ጠላት ዙሪያዬ ሲዞር ይውላል
አባባ ቅጥሬን በእሳት ቀጥሮታል
አያገነኝም ሌት ቀን ቢለፋ
የሚጠብቀኝ ኢየሱስ አያንቀላፋም
አያንቀላፋም (፬x)
አዝማች · Chorus
ነገሬን በሚያውቅልኝ በእርሱ ላይ እጥላለሁ
ትላንትን ያሻገረኝ ለነገም አምነዋለሁ (፪x)
ያኖረኛል እርሱ ያሳየኛል
ያኖረኛል እርሱ ያሳየኛል
ያኖረኛል ገና ያሳየኛል
ያኖረኛል እርሱ ያሳየኛል
ቁጥር 3 · Verse 3
ሃማ በቅናት ሞትን ደግሶ
ለመርዶኪዮስ ጉድጓድ ተምሶ
መቼ ለጠላት ታልፎ ተሰጠ
አምላኩ ደርሶ ነገሩ ተገለበጠ
ተገለበጠ (፬x)
ሰምቼ ነበረ በጆሮዬ
ሁሉን ቻይ እንደሆንክ አባብዬ
ዛሬም ዐይኔ አይታሃለች
ነፍሴ ታመሰግናለች
እንደሰማሁ እንዲሁ አየሁ (፫x) ሆ
እንደሰማሁ እንዲሁ አየሁ (፫x) ሆ
ከዘለዓለም ፍርድ ከሞት ፍርሃት
በደም ኪዳን ነው ነፍሴን የዋጃት
በላይ በረከት አንዴ ባርኮኛል
ኢየሱስ አለልኝ ኧረ እኔስ ምን ያሰጋኛል
ምን ያሰጋኛል (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ያኖረኛል እርሱ ያሳየኛል
ቁጥር 5 · Verse 5
ያኖረኛል እርሱ ያሳየኛል
ያኖረኛል ገና ያሳየኛል
ያኖረኛል እርሱ ያሳየኛል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ