Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ቅዱስ ነህ

Qedus Neh

2014 · ትራክ 1 · 5:29 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ለተቀመጥከው (፪x)

ምሥጋና አምልኮ ይኸው ይዤ መጣሁ ለአንተ ልሰዋ (፪x)

ቅዱስ ቅዱስ እያልኩኝ ወደ ማደሪያህ እገባለሁኝ

ቅዱስ ቅዱስ እያልኩኝ ወደ መቅደስህ እገባለሁኝ

ቅዱስ ነህ ቅዱስ (፬x)

ቅዱስ ነህ ቅዱስ (፬x)

ቅዱስ እያሉህ ሲያመልኩ መላዕክቱ

ክብርህ ቤቱን ሞልቶት ነበር ኦ አቤቱ

እኔም ከልቤ ቅዱስ እያልኩ እጮሃለሁ

አንተ ቅዱስ መሆንህን አውጃለሁ

ቅዱስ ነህ ቅዱስ (፬x)

አመልካሃለሁ ቅዱስ እያልኩኝ

እንዳንተ ያለ ስላላየሁኝ

ቅዱስ ነህ ቅዱስ (፬x)

ለዘለዓለም ዙፋንህ ላይ ተቀምጠሃል

ደፍሮ ከዙፋንህ ና ውረድ ማን ይልሃል

አይቆጠርም ዘመናትህ አንተ ጌታ

ቅዱስ እያልኩኝ ልስገድልህ በዕልልታ

ቅዱስ ነህ ቅዱስ (፬x)

ይደርደርልህ ዛሬም በገናው

በዕልልታ ሆታ ቅኔ ምሥጋናው

ቅዱስ ነህ ቅዱስ (፬x)

ስራህ ትክክል እውነተኛ እንከን የለህ

ነውር ነቀፋ የሌለብህ አንተ እኮ ነህ

ፍርድ አታጓድል አታደላ ጻድቅ አምላክ

ነፍሴ ሁልጊዜ በምሥጋና አንተን ትበል

ቅዱስ ነህ ቅዱስ (፬x)

የጌታዎች ጌታ ጌታ ጌታ የነገሥታት ንጉሥ

የአማልክት አምላክ አምላክ አምላክ የእስራኤል ቅዱስ

ልዑል እግዚአብሔር ስምህ ይወደስ

ስምህ ይቀደስ ዛሬም ልዘለዓለም

ይወደስ ክቡር ስምህ (፪x)

ይቀደስ ክቡር ስምህ (፪x)

ይወደስ ክቡር ስምህ (፪x)

ይቀደስ ክቡር ስምህ (፪x)

ይወደስ ክቡር ስምህ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ