ሃገሬ
Hagerie
2014 · ትራክ 14 · 5:13 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
"እሄዳለሁ ሃገሬ ጌታዬን አየዋለሁኝ
ላየው ፊትለፊቱ"
ቁጥር 2 · Verse 2
ሃገር አለኝ እኔስ በሠማያት
በጉ ብርሃኗ የሆነላት የሆነላት
ሃገር አለኝ እኔስ በሠማያት
የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ያዘጋጃት (፫x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እንግዳ ነኝና አልሆንም ቤተኛ (፪x)
ሃገሬ ሠማይ ነው በላይ ርስት አለኛ በላይ ቤት አለኛ
ተዘጋጅቼ ልጠብቀው ቤቴን ሌት ተቀን ላሰናዳው
ይመጣል ጌታ ይመጣል ፤ ይመጣል እርሱ ይመጣል (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
አሃሃሃ አልዘናጋም አሃሃሃ ጠፊውን አይቼ
አሃሃሃ በላዬ ላከማች አሃሃሃ ልስራ ተግቼ
አሃሃሃ እርሱ ይመጣል አሃሃሃ ወይ እሄዳለሁ
አሃሃሃ እንደስራዬ አሃሃሃ እቀበላለሁ
ቁጥር 5 · Verse 5
ዐይን ያላያት የሰው እጅ ያልሰራት
ለልጆቹ ጌታ ያዘጋጃት
ቁጥር 6 · Verse 6
ሃገር አለኝ እኔስ በሠማይ (፪x)
የቅዱሳን የጻድቃን ከተማ
ቀኑ ቀርቧል ወደዚያ ልገባ
ሃገር አለኝ እኔስ በሠማይ (፪x)
ቁጥር 7 · Verse 7
መታረት መራቆት መራብም ያልፍና
ሰቆቃው ሃዘኑ ሁሉ ይረሳና
ጌታዬን ፊትለፊት በክብር አያለሁ
ናፍቆቴን ደስታዬን ያኔ እወጣለሁ
አዝማች · Chorus
ይመጣል ጌታ ይመጣል
ይመጣል እርሱ ይመጣል (፪x)
ቁጥር 8 · Verse 8
የፍጻሜው መለከት ይነፋል
ጌታ ኢየሱስ በክብር ይመጣል
ቁጥር 9 · Verse 9
ሃገር አለን እኛስ በሠማይ (፪x)
በቅጽበት ዐይን ሁሉ ይለወጥና
እንሄዳለን ልንኖር ከእርሱ ጋራ
ሃገር አለን እኛስ በሠማይ (፪x)
ቁጥር 10 · Verse 10
የዚህ ዓለም ነገር አላፊ ጠፊ ነው
ውበት ደም ግባትም ሁሉ ረጋፊ ነው
ጌታዬ ሲመጣ እንዳየው ሳላፍር
ሥጋዪን ልጐስም ልኑር ለእርሱ ክብር
አዝማች · Chorus
ይመጣል ጌታ ይመጣል
ይመጣል እርሱ ይመጣል (፪x)
ቁጥር 11 · Verse 11
እዚህ ነዋሪ አይደለሁም አይደለሁም
እንግዳ ነኝ እኔ
ቆይታዬ ያበቃና ይፈጸማል እሄዳለሁ ሃገሬ
ቁጥር 12 · Verse 12
ሃገሬ በሠማይ ሃገሬ
ሃገሬ በላይ ነው ሃገሬ
ሃገሬ በሠማይ ሃገሬ
ሃገሬ በላይ ነው ሃገሬ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ