ክብሬ
Kebrie
2014 · ትራክ 11 · 5:39 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በምሥጋና ወደመቅደሱ እገባለሁ
ከልቤ ሆኜ እቀኛለሁ
ያከበረኝን ሰው ያረገኝን
አምላኬን አመልከዋለሁ
በምሥጋና ወደመቅደሱ እገባለሁ
ከልቤ ሆኜ እቀኛለሁ
የወደደኝን አዎ የሞተልኝን
ኢየሱሴን አከብረዋለሁ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ኢየሱስ (፬x)
ኢየሱስ ኢየሱስ (፬x)
ኢየሱሴ ክብሬ ማረጌ
ኢየሱሴ የአብ ስጦታ
ኢየሱሴ ነህ ዝርግፍ ጌጤ
ኢየሱሴ ውበቴ ጌታ
ኢየሱሴ የምትወደድ
ኢየሱሴ ፍቅር እኮ ነህ
ኢየሱሴ አሳዳጊዬ
ኢየሱሴ ይቧረክ ስምህ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የሚያንኳኳ መልስ ሽቶ ማን አፈረ አንተን ጠርቶ
ማን አፈረ አንተን ጠርቶ (፪x)
ልመናውን ሰማህለት ሸክሙን አንተ ወሰድክለት
ሸክሙን አንተ ወሰድክለት (፪x)
ተደንቂያለሁ በማዳንህ
ተነገሮ አያልቅም ድንቅ ስራህ
መፍቻው ተገኝቶ የእንቆቅልሹ
ሌላ ሰው ሆኗል ዮሴፍ ትንሹ
ተዐምር ነው ስራህ ጌታዬ
ከፍ በል በምሥጋናዬ
ድንቅ ነው ስራህ ጌታዬ
ከፍ በል በምሥጋናዬ
ከፍ በል በምሥጋናዬ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የቱን ትቼ የቱን ላውራ
ኢየሱሴ የአንተን ስራ (፪x)
ባይመጥንም ምሥጋናዬ
ይኸውልህ አባብዬ (፪x)
ሰው የናቀውን የገፋውን መቼ ተውከው ብቸኛውን
መቼ ተውከው ብቸኛውን (፪x)
አከበርከው በአደባባይ ትዕዛዝ ወጣለት ከሠማይ
ትዕዛዝ ወጣለት ከሠማይ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
አይቻለሁኝ ስትረዳ
ከጐኑ ስትሆን ለተጐዳ
እጄን በእጆችህ ይዘህ መራህ
ያልገመትኩትኝ ክብር አሳየኸኝ
ማረጌ ክብሬ ኢየሱሴ
ላምልክህ ከልብ ከነፍሴ
ማረጌ ክብሬ ኢየሱሴ
ላድንቅህ ከልብ ከነፍሴ
ላምልክህ ከልቤ ኢየሱሴ
ላምልክህ ከልብ ከነፍሴ
አዝማች · Chorus
ኢየሱሴ የመዳን ቀንዴ
ኢየሱሴ መታመኛዬ
ኢየሱሴ አንተ ነህ ውዴ
ኢየሱሴ ወንድም ጋሻዬ
ኢየሱሴ ምትክም የለህ
ኢየሱሴ የፍቅር ምርጫዬ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ