ቅድስና
Qedesena
2014 · ትራክ 6 · 5:27 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ክርስትናን መኖር መኖርን እሻለሁ
ጥማቴም ጸሎቴም አንተን ለመምሰል ነው ጌታ
ተቀድሶ መኖር መኖርን እሻለሁ አው
ጥማቴም ጸሎቴም አንተን ለመምሰል ነው አባ
አዝማች · Chorus
እቀደሳለሁ (፫x) ክብርህን ላየው ጌታ
እቀደሳለሁ (፫x) ፊትህን ላየው አባ
ቁጥር 2 · Verse 2
እስኪ አግዘኝ አቅም ስጠኝ
ለአንተ እንድኖር አስጨክነኝ
አስጨክነኝ አስጨክነኝ
አስጨክነኝ አባ አስጨክነኝ አዎ
ቁጥር 3 · Verse 3
ዓለምን በጽድቅህ ስራ እየኮነንኩኝ እህ እይኮነንኩኝ
ልኑር አንተን ኢየሱሴን እያስከበርኩኝ አዎ እያስከበርኩኝ
ቅዱሱ ስምህ በእኔ ስለተጠራ አባ ስለተጠራ
በእኔ እንዳታፍርብኝ (ስምህን እንዳላሰድብ) እርዳኝ አደራ አዎ እርዳኝ አደራ
ቁጥር 4 · Verse 4
ጉልበት ስጠኝ አቅም ስጠኝ
በጽድቅ እንድኖር አስጨክነኝ
አስጨክነኝ አስጨክነኝ
አስጨክነኝ አባ አስጨክነኝ አዎ
ቁጥር 5 · Verse 5
ጨለማ ለዋጣት ዓለም ብርሃን ሆኜ እህ ርሃን ሆኜ
ለትውልድ ምሳሌ አርገኝ ልኑር ጨክኜ አዎ ልኑር ጨክኜ
መራራውን አጣፋጭ የምድር ጨው አርገኝ አባ የምድር ጨው አርገኝ
ሁልጊዜ የጽድቅህ ፍሬ አይታጣብኝ አዎ አይታጣብኝ
ቁጥር 6 · Verse 6
እስኪ አግዘኝ አቅም ስጠኝ
ለአንተ እንድኖር አስጨክነኝ
አስጨክነኝ አስጨክነኝ
አስጨክነኝ አባ አስጨክነኝ አዎ
ቁጥር 7 · Verse 7
ቅድስና ለእግዚአብሔር ቅድስና (፬x)
ለጊዜው ለሚገኝ ደስታ ራሴን አልሸጥም አሃ ራሴምን አልሸጥም
ለኑሮ ለእንጀራ ብዬ አልሸቃቅልም አዎ አልሸቃቅልም
ይራበኝ እንጂ ልጣ ሁሉ ይቅርብኝ አዎ ሁሉ ይቅርብኝ
ጨክኜ ላገለግልህ ወስኛለሁኝ አዎ ወስኛለሁኝ
እንደልብህ ልኑርልህ
በእኔ ጌታ ደስ ይበልህ
ከአንተ ጋራ አሃ እኖራለሁ
ክብርህን ላይ ናፍቄያለሁኝ
አዝማች · Chorus
እቀደሳለሁ (፫x) ክብርህን ላየው ጌታ
እቀደሳለሁ (፫x) ፊትህን ላየው አባ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ