ፍቅር
Feqer
2014 · ትራክ 4 · 6:18 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እንደበግ ሲነዳ አሁን አልከፈተም
ወስደው ሲያንገላቱት አንዳች አልመለሰም (፪x)
አዝማች · Chorus
አስጨነቁት በጅራፍ ገረፉት
በአደባባይ እርቃኑን ሰቀሉት
ቤዛ ሆነ በእኔ ፈንታ ስለእኔ ተመታ
ፍቅር ጐልጐታ ላይ
ፍቅር ቀራኒዮ ላይ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እዩት እየሲሴን እዩት ስቃዩ ሲያይል
እዩት አባብዬን እዩት ሲቃዩ ሲያይል
ስቃዩ ሲያይል (፬x)
አዝማች · Chorus
ለእኔ ነው ይህ መንከራተቱ
ለእኔ ነው ስቃይን ማየቱ
ለእኔ ነው ሲዘባበቱበት
ለእኔ ነው የበዛው ትዕግሥቱ
ለእኔ ነዋ ደፋ ቀና ያለው
ለእኔ ነዋ የደም ላብ ያላበው
ለእኔ ነዋ ህመሜ ያመመው
ለእኔ ነዋ በጦር የተወጋው
ለእኔ ለእኔ ለእኔ ነዋ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አባት ሆይ ፈቃድህ ያልከው ይሁን ብሎ
መራራውን ጽዋ ጠጣው ተንጠልጥሎ (፪x)
አፈረሰው የጥሉን ግድግዳ አስታረቀን እኛን ከአብ ጋራ
ኢየሱሴ ጣልቃ ገብቶ አንድ አደረገን ሞቶ
አዝማች · Chorus
ለእኔ ነዋ ኤሎሄ ኤሎሄ
ለእኔ ነዋ ብሎ የዋተተው
ለእኔ ነዋ ጀርባውን በጅራፍ
ለእኔ ነዋ የተተለተለው
ለእኔ ለእኔ ለእኔ ነዋ (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የድካሙን ዋጋ ፍሬውን ሊያይ
ታገሰ መስቀል ላይ ሲቀበል ስቃይ (፪x)
የተናቀ ደግሞም የተጠላ
የህማም ሰው መሰለ ተላላ
በቁስሎቹ ተፈውሻለሁ ሕይወት አግኝቻለሁ
አዝማች · Chorus
ለእኔ ለእኔ ለእኔ ነዋ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ