ይሆናል
Yehonal
2014 · ትራክ 8 · 6:14 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የቀድሞውን ነገር አላስብም
አሮጌው ሁሉ አልፏል ሁሉ አልፏል
ተፈጠመ ያየጥንቱ ታሪክ ዘመን መጥቶልኛል
የቀድሞውን ነገር አላስብም
አሮጌው ሁሉ አልፏል ሁሉ አልፏል
የእንባው ጊዜ ታሪክ ሆኖ ሊቀር ቀን ተቀጥሮለታል
ቁጥር 1 · Verse 1
እነሆ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ
እርሱንም አሁን አበቅለዋለሁ
ያለኝ ጌታ ያለኝ ጌታ
የተናገረኝን ያደርገዋል ያደርገዋል አምነዋለሁኝ
አምነዋለሁኝ (፬x)
አዝማች · Chorus
ይሆናል አዲስ ነገር
አያለሁ አንድም አይቀር
ይሆናል አዲስ ነገር
አያለሁ አንድም አይቀር
የተናገረኝ ጌታ ሰው አይደል ሚያመነታ
ቃል ወጥቷልና ከእርሱ ያደርገዋል ንጉሡ
ይሆናል ይሆናል ጌታ ያለው ይሆናል
ይሆናል ይሆናል እርሱ ያለው ይሆናል
(አዲስ ነገር ይሆናል አዲስ ነገር አዲስ ነገር)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሽንፈት አላወራም ድል አለ ከፊቴ
ኃይል የእግዚአብሔር ነው ይሄ ነው ትምክቴ
የነሃሱ ደጃፍ አውቆ ይከፈታል
እግዚአብሔር ሲነሳ ኧረ ማን ይቆማል
ይሆናል ይሆናል ጌታ ነው ይሆናል
ይሆናል ይሆናል እርሱ ያለው ይሆናል
ቁጥር 3 · Verse 3
ዐይኖች ያላዩትን ጆሮም ያልሰማውም
ከሰዎች ዘንድ ከቶ ያልተገመተውን
እንግዳ ነገርን አምላኬ ያደርጋል
አዲስ አዲስ ነገር በሕይወቴ ይሆናል
ቃል አለኝ ቃል አለኝ እኔ
ይሰራል አያለሁ በዐይኔ
ቃል አለኝ ቃል አለኝ እኔ
ይሰራል አያለሁ በዐይኔ
አያለሁ በዐይኔ (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ምድረ በዳ ቢሆን አንተ ያለህበት
አትፍራ ወንድሜ ጽና በቆምክበት
ጻድቁ እግዚአብሔር እንዴት ይጥልሃል
ታሪክን ገልብጦ ገና ያቆምሃል
ተስፋ የሰጠህ የታመነው የታመነው
ሁሉን ይሰራል ኤልሻዳይ ነው ኤልሻዳይ ነው
ተስፋ የሰጠህ የታመነው የታመነው
ሁሉን ይሰራል ኤልሻዳይ ነው ኤልሻዳይ ነው
ቁጥር 5 · Verse 5
አምናለሁ እርሱ ታማኝ ነው
ጌታዬ እርሱ ታማኝ ነው
ይሰራል እርሱ ታማኝ ነው
ያደርጋል እርሱ ታማኝ ነው
ምድር ብታልፍ ሠማይ ቢያልፍ
ቃሌ ግን አያልፍም ያለው
ጌታ እኮ ነው ጌታ እኮ ነው (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ኧረ የምን ሥጋት ለምን ፍርሃት
ሁሉን ቻይ አምላክ
አለኝ አባት
ትዕዛዝ ከሠማይ ከአምላኬ ወጥቶ
እንዴት ይሆናል አልልም ከቶ
አልልም ከቶ (፬x)
አዝማች · Chorus
ቃል አለኝ ቃል አለኝ እኔ
ይሰራል አያለሁ በዐይኔ
ቃል አለኝ ቃል አለኝ እኔ
ይሰራል አያለሁ በዐይኔ
አያለሁ በዐይኔ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ