Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የማዕዘን ራስ

Yemaezen Ras

2014 · ትራክ 13 · 4:22 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ኢየሱስ ከስም ሁሉ በላይ ስሙ ኃያል

ጉልበት ሁሉ ፊቱ ተንበርክኮ ለእርሱ ይሰግዳል

አይቆምም ማንም ፊቱ እሳት ነው ለጠላቱ

አምላኬ ክንደ ብርቱ

ኢየሱስ ክንደ ብርቱ ፤ የሱሴ ክንደ ብርቱ

ጌታዬ ክንደ ብርቱ ፤ ኢየሱሴ ክንደ ብርቱ

አሃ ለተቀበሉት አሃ በእርሱ ለሚያምኑት

የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ስልጣን ሰጣቸው

ጌታዬ ስልጣን ሰጣቸው ፤ ኢየሱስ ስልጣን ሰጣቸው

ጌታዬ ስልጣን ሰጣቸው ፤ አሃ ስልጣን ሰጣቸው

ግንበኞች የናቁት ድንጋይ

እርሱ የማዕዘን እራስ ሆነ

እርሱ የማዕዘን እራስ

እርሱ የማዕዘን እራስ ሆነ

እርሱ የማዕዘን እራስ

ከስም በላይ ስምን ሰጥቶ

እግዚአብሔር ያለልክ ያከበረው

ኢየሱስ እርሱ ጌታዪ ነው

ኢየሱስ እርሱ ንጉሤ ነው

ኢየሱስ እርሱ አባቴ ነው

ኢየሱስ እርሱ አዳኜ ነው

ያድናል የሚጠራውን ያድናል የታመነውን

ያድናል በልቡ ዙፋን ያድናል ያነገሠውን

ኢየሱስ ከሞት የማምለጫ ጽኑ አለት

ሰው ሁሉ ስሙን እየጠራ ሚድንበት

ሕይወት ነው የዘለዓለም የሚያድን ከጠፊው ዓለም

ከእርሱ በቀር ማንም የለም

ሕይወት ነው የዘለዓለም ከእሱ በቀር አዳኝ የለም

ንጉሥ ነው ለዘለዓለም ከእርሱ በቀር አዳኝ የለም

አሃ ለተቀበሉት አሃ በእርሱ ለሚያምኑት

የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ስልጣን ሰጣቸው

ጌታዬ ስልጣን ሰጣቸው ኢየሱስ ስልጣን ሰጣቸው

ጌታዬ ስልጣን ሰጣቸው አሃ ስልጣን ሰጣቸው

ይሄ ስም ነው መዳኛዬ

በክፉ ቀን ማምለጫዬ

ኢየሱስ ነው መዳኛዬ

በክፉ ቀን ማምለጫዬ (፫x)

ከእርሱ በቀር ሌላ ላላይ ሌላ ሌላ ላላይ

ሾሜዋለሁ በላዬ ላይ እኔስ በላዬ ላይ

ሌላ ሌላ ላላይ (ሌላ ሌላ ላላይ) (፮x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ