ትልቅ ነህ
Teleq Neh
2014 · ትራክ 9 · 6:14 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ዝናህን ላውራ ኦሆሆሆ ታላቅነትህን
ስላንተ ዝና አውርቼ አልጠግብም
አዝማች · Chorus
ብናገር ብናገር (፪x)
ኦ እግዚአብሔር ትልቅ ነህ
አንተ እግዚአብሔር ትልቅ ነህ
ኦ እግዚአብሔር ትልቅ ነህ
አንተ እግዚአብሔር ትልቅ ነህ
ትልቅ ነህ (፬x)
ትልቅ ነህ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ቀና ብዬ ሠማዩን ሳይ
ጨረቃዋን ከዋክብቱን ሳይ
አሻቅቤ ተራራውን ሳይ
ባሕሩን ውቅያኖሱን ሳይ
አፈጠጠሩ ይገርመኛል
አቤት ውበቱ ይደንቀኛል
ጌታዬ የአንተን ትልቅነት ያሳየኛል
አመልክሃለሁ እጆቼን አንስቼ
አመልክሃለሁ ፊትህ ተደፍቼ
አመልክሃለሁ ክብሬን ሁሉ ትቼ
አመልክሃለሁ ወድጄ ፈቅጄ
አዝማች · Chorus
ኦ አንተ ታላቅ ነህ እኔም አላውቅህም (፪x)
ኦ አንተ ታላቅ ነህ እኛም አናውቅህም (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ
የማትመረመር መርማሪ
ጥበብህን ዕውቀትህን ማን ያውቀዋል
ፍርድህም ከማስተዋል ሁሉ ይልቃል
ኦ ለመንገድህ ፍለጋ የለው
አደራረግህ እጅግ ጥልቅ ነው
አቤቱ ስራህ ከአይምሮ በላይ ነው
አዝማች · Chorus
ትልቅ ነህ (፬x)
ትልቅ ነህ (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ውሆችን በእፍኝህ የሰፈርህ
ተራሮችን በሚዛን የመዘንህ
ሠማዩን በስንዝር የለካህ
የምድርን አፈር ሰብስበህ የያዝህ
ሁሉን ስትሰራ ማን አማክሮሃል
የፍርድን መንገድ ማን አስተምሮሃል
አቤት ጥበብህ ከሁሉ ይልቃል
አዝማች · Chorus
ኦ አመልካህለሁ አሃ አመልክሃለሁ
አሁ አመልክሃለሁ ጌታ አመልክሃለሁ
ኦ አመልካህለሁ አባ አመልክሃለሁ
አሁ አመልክሃለሁ ጌታ አመልክሃለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ